ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ ✍️✍️✍️ " " እኔ በፊትህ መቆሞ ባልችልም በፅድቅ ሚዛን እየፀፀታት ልቤ… — ግጥም 🇪🇹 — TG.ME

ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ

✍️✍️✍️

"
"

እኔ በፊትህ መቆሞ ባልችልም
በፅድቅ ሚዛን እየፀፀታት ልቤ ተሰብራ

በርጠሚዎስን ከንቱ ይመስል
ዛሬ ካልሆነ ብዬ ማስቸግር አይኔ ካልበራ

ከምኞት ይልቅ
ፈቃድህ ሆኖ ትፈፅመው ዘንድ እስከምታደል

ምርኩዝ ጨብጬ
ጭፍን ስራመድ ዳር ዳሩን እንጂ ባላይም ገደል

ጥውልግ ተስፋዬን
አለምልመኸው ከወደኩበት እንደተነሳው

እንደ መፃጉ
እልፍ ውለታህን ቀለል አድርጌ ስለምረሳው

ከተሳሳቱ እርምጃዎቼ
ቀናውን መንገድ በል ምራኝና የእውነት አቅጣጫን

አንተ ጠቢብ ሆይ
ታምር የሰሩ ውብ እጆችህን በራሴ ላይ ጫን
❤15
February 7, 2026 2.9K 3