፡
ሆነሽ ሳለ
ቆንጂዬ ልጅ
'ምታሳሳ 'ምትወደድ
ቢኖርሽም አፍቃሪ ልብ
መልካም ሀሳብ ቀና መንገድ
ወትሮ እኔን መንከባከብ
ባይታክትሽ ማስደሰቱ
እውነት እውነት እልሻለሁ
ማፍቀር ላልችል ደከምሽ እቱ
እያሰብኩኝ የሆንሽውን
እየታየኝ ውበት መልክሽ
ያለሽን ግልፅ ፅኑ አቋም
የሚደነቅ ፀባይ ልክሽ
እየጣርኩኝ ላለማጣት
ካንቺ ደጃፍ እግሬ እንዳይቀር
ላይሆንልኝ ደከምኩ እንጂ
አይቻልም ታግሎ ማፍቀር
Join
👇👇👇👇
https://t.me/getmtg
Telegram
የግጥም ጥግ
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።
የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ
ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት
በ @Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።

3
2February 2, 2026 2.9K 5