ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ ‎✍️✍️✍️ ‎ ‎ የከረመ ናፍቆት ‎###### ‎" ‎" ‎" ‎ ልክ እንደ… — ግጥም 🇪🇹 — TG.ME

ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ
✍️✍️✍️

‎ የከረመ ናፍቆት
‎######
‎"
‎"
‎"
‎ ልክ እንደ ህፃናት
‎የዋህ ሁን የሚል ቃል ሰመመን ያነቃው
‎***
‎የሞተች እናቱን ገበያ እንደ ሄደች
‎ቆሞ ሚጠብቃት እስክትመጣ ናፍቃው
‎****
‎ ደጅ ደጁን ሲቃኝ
‎ልቡ ያላረፈው በምንም ባይተካት
*
‎ የሚያሳሳ ገፁን
‎ በእምባ ዶፍ አጅቦ
‎ይጠብቃት ነበር ቀሚሷን ለመንካት
‎****
‎ደሞ,,,,
‎ ሀዘን ላጠላበት
‎የዘመናት ፍቅሩን ላልገደበው ወሰን
*
‎ እንዲህ ሲል ጠየቀው
‎ ግድ የለም እማዬን
‎ህይወት እንዝራባት በጭቃ ለውሰን
**
‎ ለጥያቄው ክብደት
‎የሚመጥን ቃላት ቢያጣ በቂ መልስም
*
‎ ከእንግዲህ በኃላ
‎እናትህ ፈፅሞ በቃ አትመለስም
*
‎ ብሎ እንዳያረዳው
‎መቼም ያባት ነገር የልጅ ገላ አሳሳው
***
‎ እንዳይዋሸው ደሞ
‎መሸከም ከበደው ጉልበት አቅም ነሳው
*
‎ታዲያ በዚህ መሀል,,,,,,,

‎ የተነገረውን የማይካድ እውነት
‎በውስጡ አዳፍኖ ያከረመው ሚስጥር
*
‎ አንድ ነገር ያውቃል
‎ከአፈር እንደ ሆነ አምላክ ሰው ሲፈጥር
‎****
‎ ተፈጥሮ ብትቸረው
‎የመውደድን እውቀት የፍቅርን ጥልቀት
‎***
‎ ደርሶ እንደሚባለው
‎ከያዘ እንደማይለቅ ልጅ እና ወረቀት
‎***
‎ ከመፍጠርህ በፊት
‎እልፍ ዘመናትን እንደ ተቀዳጀህ
‎****
‎ ካፈር ብናኝ ዘግነህ
‎በጭቃ ለውሰህ ፍጥረትን ያበጀህ
‎***
‎ የሰናፍጭ ታህል
‎እምነት ባይኖረውም እንዳይጠራጠር
‎***
‎ለህፃን ልጅ ስትል ሁለት እናት ፍጠር
‎****
‎ሁሉን ቻይ ነህና ስለምታውቅበት
‎ካንዷ ሽጉጥ ይበል አንዷ ስትሞትበት


❤23🥰2🔥1
October 12, 2025 4.9K 27