ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ ✍️✍️✍️ ". " " መጨረሻው ይሆን ????? ✍️✍️✍️✍️ መንግስትም በመንግስ… — ግጥም 🇪🇹 — TG.ME

ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ
✍️✍️✍️
".
"
"
መጨረሻው ይሆን ?????

✍️✍️✍️✍️

መንግስትም በመንግስ ላይ
እንዳሻው እየተነሳ በክፋት ደርሶ ቢያምፅም
###
ዘላለም ያለና ሚኖር
ቃልህም በተግባር ታየ ትምቢቱን በኛ ልትፈፅም
###
ጥላቻ እያደባየ
ነፃነት ፍቅርና ሰላም ሰንብቷል ከደፈረሰ
###
ምድሪቷም ጭንቅ ብሏታል
ማምለጫ መግቢያ የጠፋት ምፀአት እንደ ደረሰ
###
ባቢሎን በኛ ሲደገም
ተመልከት ዓለም ታምሳ ሲያጋያት ግዙፍ ሚሳኤል
###
ኢትዬጵያ እጇን ዘርግታ
ትማፀን ትለምን ነበር ኃያሉን ቅዱስ ሚካኤል
###
አውቃለው ትወደን የለ
በከንቱ ጠፍተን እንዳንቀር ልጅህን ጠብቅ ከክፉ
###
ሰይፈኛን የሚያንበረክክ
አብሳሪ መልአክ ልከህ ከልለን ጋርደን በክንፉ
###
ወይ እንደ ሰብዓ ሰገል
በተስፋ ምርኩዝ ተመርተን በዳዊት አመልካች ኮከብ
###
ይህንን የጥፋት ዘመን
በጥበብ ዳግም አሻግረን ተውሰህ የኖህን መርከብ
❤14🥰3
July 21, 2025 5.2K 5