(ያሬዳዊ ግጥም)
✍️✍️✍️✍️
የስመኘው ማስታወሻ
"
"
"
ግሽ አባይ ግሽ አባይ
ግድ የለሽም ተይ ግሽ
የሞተልሽ ጀግና እያለ
ክፉ ገዳይ ምታንግሽ
እድሜ ጠገብ የሆንክ አንተ
ማደሪያህን አርገህ የትም
ስንት ዘመን ስትባክን
ያልቀለስከው ጎጆ ቤትም
አንድ ቦታ የማይረጋ
ቅጠል አልባ ስር የለሽ ግንድ
ስንት ዘመን ስትዞረው
ተሸክመህ በተስፋህ ክንድ
ስትማስን ስባክነው
ላንዱ ሲሳይ ሆነህ ጌጥም
በምሳሌ ተረት ተረት
ያባይን ልጅ ሲገለው ጥም
እንዲ ሲባል አለሰማህም
እርግጥ አንተ አልጠማህም
ሆድ አደሮች ሲያደባዩ
ላንተ ጅረት ካራ ስለው
የሚፋፉ ያረም እምቦጭ
በቀጤማ ተመስለው
ለመንገድህ ተነጥፈው
ከሳሎንህ ተጎዝጉዘው
ባሙቁልኝ ያሆ እጃቸው
ላንተ መጥፊያ ስለት መዘው
አላየህም አልሰማህም?
በርግጥ አንተ አልጠማህም
ለሀገሩ ለወገን ሲል
አንድ ህይወቱን ለገበረ
በመጠየቅ ለሚያምን ልብ
ምላሽህስ ምን ነበረ
ልጠይቅህ መልስልኝ
እርሜን ላውጣ ባንዲት ስንኝ
ክንደ ብርቱ ሳይበገር
ከተሰዋ ለቢሊዮን
የዚን ሰው ሀቅ መልስ
እባክህን አንተ ግዮን

12
1
1July 16, 2025 4.8K 5