ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ ✍️✍️✍️ የተሰበረ ልብ "።።።።።።።" " በታካሚ ጫማ ረጅሙን ጉዞ ላልተራመደ… — ግጥም 🇪🇹 — TG.ME

ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ
✍️✍️✍️

የተሰበረ ልብ
"።።።።።።።"
"
በታካሚ ጫማ
ረጅሙን ጉዞ
ላልተራመደ እግር
###
በሐኪም መነፅር
አሻግሮ ላላየ መከራና ችግር
###
በሞት'ና ህይወት
መካከል ላለ ሰው
ተስፋ እየለገሰ
###
ከፈጣሪ በታች
ህሙማን ለመርዳት
ሐኪም ከደረሰ
###
በኑሮ ውድነት
አቅሉን ያጣ ሰው
ማወቅ መች ይገዳል
###
ሰማይ የቀረበው
ዙፋን ላይ ተቀምጦ
በጭፍን ይፈርዳል
###
ቢሆንም ግን ዳሩ,,,,,
"
"
ደከመኝን ሳያውቅ
ቀን ከሌት ሲለፋ
ለሀገር ለወገን እያሰበ ነገን
###
ላቡን ጠብ አድርጎ
አንድም ሳይጠየፍ
የተሰበረውን አሽቶ ለመጠገን
###
ግዳጁን ተወቶ
መብቱን በጠየቀ እንዲፈፀምለት
###
ያን ጊዜ ነው መፍራት
ከታካሚው ይልቅ ሐኪም ያመመው ለት
###
በየ ጤና ጣቢያው
በየሆስፒታሉ ታሞ ከሚያጣጥር
###
በኑሮ ውድነት
የሚሞተው ሐኪም ይበዛል በቁጥር
❤16🙏8👍4👏1
May 25, 2025 5.7K 23