ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፏል።
በሴቶች የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ አንድ ጨዋታዎች ከተጠናቀቁ በኋላ ንግድ ባንክ ከምድብ ማለፉን አረጋግጧል።
አስቀድሞ የነበረው የውድድሩ ደንብ አራት ቡድኖችን ከያዘው ምድብ አንድ ሁለት ቡድኖች ሶስት ቡድኖችን ከያዙት ምድብ 2 እና 3 ደግሞ አንድ አንድ ቡድኖች ያልፋሉ የሚል ነበር።
ነገር ግን ውድድሩ ከተጀመረ በኋላ በተሻሻለው ደንብ መሰረት ከሶስቱም ምድቦች አንደኛ ሆነው ያጠናቀቁ ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፈው ከሶስቱ ምድቦች ጥሩ 2ኛው አራተኛው የግማሽ ፍፃሜ ቡድን ይሆናል።
በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅዳሜው ጨዋታ ያስቆጠራቸውን 11 ግቦች ተከትሎ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል።
ነገ በሚደረገው የምድቡ ጨዋታ ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ የጅቡቲውን ዩጄኮ ካሸነፈ ወይም አቻ ከተለያየ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግማሽ ፍፃሜው ከራሱ ከካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ ጋር ይገናኛል።
ዩጄኮ ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስን ማሸነፍ ከቻለ ደግሞ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዩጄኮ ጋር ለፍፃሜ ለማለፍ ይጫወታል።
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታው ቅዳሜ 07:00 ጀምሮ ይደረጋል።

3
1August 25, 2026 1.3K 1