በተለይ በአሁን ወቅት አንድ ደሃ ድንገት ተነስቶ ሀብታም ሊሆን አይችልም:: በምርቃናም በጠንካራ ሠራተኝነትም የሚደረስበት አልሆነም:: መመርቀን (ሞቲቬት መሆን) ጥሩ ነው:: ጠንካራ ሠራተኝነትም መጥፎ ሆኖ አያውቅም:: ግን በጥበብ መሆን አለበት:: አንድ ኢትዮጵያዊ ደሃ በ10 ዓመት እንዴት ወደ ፋይናንስ ነጻነት ሊሻገር ይችላል? የሚል ፍኖተ ካርታ ነው:: የመጀመሪያው ዓመታት ላይ ብሩን ልቆጥብህ ቢልም የማይሆን ስለሆነ በራሱ ላይ ቢቆጥበው ማለትም ቢበላበትና ቢቅምበት ይሻላል ማለት ሳይሆን አጫጭር የሙያ ስልጠናዎችን ቢወስድበት በሚል ተነሳሁ:: ኤሌክትሪክ, ቀለም, ሜካኒክ, ሹፍርና, የጸጉር ሙያ, IT, Ai, ወዘተ ስልጠናዎችን ወሰደ ማለት ወጥቶ ባይሠራበት እንኳ ቤት ውስጥ ለራሱ ቢሠራ ወጪ ቀነሰ ማለት ነው:: ስቶቭ በተበላሸ ቁጥር አዳዲስ አይገዛም:: ምን የኤሌክትሪክ ዝርጋታ እንደሚያስፈልግ ያውቃል:: እንዲሁም ሙያ ካለው በየትኛውም circumstances ተቋቁሞ መውጣት ይችላል:: የተለያዩ ሙያዎች ካሉህ ሁሌ ሥራ ላይ ነህ:: ስትሠራ ወጪ ማውጫ ጊዜ የለህም:: ይልቅስ ገቢ ላይ ነህ:: ስለዚህ ይህንን የበዛ ገቢ ወደ ጊዜያዊ ቁጠባ ብትወስደው ግሽበት ብዙም አያጠቃውም:: በቅርብ ርቀት ወደ ንብረት ትቀይረዋለህ:: ዝርዝሩን ከመጽሓፎቹ!
የታዳጊዎቹ ገጹም ትንሽ ነው:: በልጆች አቅም ነው የተዘጋጀው:: የአዋቂዎቹ ይሰፋል::
23
4
4September 2, 2026 1.6K 2

