ተጽፎ እጃችሁ እስኪደርስ
ያለውን ፈተና ልቀንጭብ
==============
👉🏼 ሳይንስ ዘርፍ ላይ መጽሓፍ ማዘጋጀት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ የጻፈ ያውቀዋል::
👉🏼 ከዚያም ለድፍን ሀገር በነጻ ነው የማሰራጨው:: ዱዲ አምስት ሳንቲም ለሥርጭት አልተቀበልኩም:: ይልቅስ እከፍላለሁ ሁላ::
👉🏼 ምክንያቱም ጽፌ ሳልጨርስ, ማተሚያ ቤት ሳላስገባ ጨርሶ ለሚከፍለኝ ሰው ብችል በየቤቱ እራሴ ባደርስ ለኔ ክብር ነው:: ለዚህ ሥራ ብር ብቻ ሳይሆን በትክክል መረጃ የሞሉልኝ በጣም ረድተውኛል::
👉🏼 ወይኔ በላቸው ወይኔ በላቸው!! ከሌላ ባንክ እና ከቴሌብር ገንዘብ ብቻ የላኩ ሰዎችን መረጃ ማሟላት የቻልኩት ኦዲተር እና የሒሳብ ሰነድ አጣሪ ሆኜ ስለሠራሁ ይመስለኛል የተወጣሁት:: ከየት በማን አማካኝነት ለምን እንደገባ ከማይታወቅ የብር ተመሳሳይ ቁጥሮች ተነስተህ የሰውየው ማንነት ጋር ለመድረስ ያለው መከራ ለማውራት አይመችም:: 900 ብር ሲል ለምን? Really የመጽሓፍ ነው? ከቴሌብር እና Other Bank የመጣው ምንም Clues የለውም::
👉🏼 ፌስቡክ ኮሜንት ላይ ማንነቱ በማይታወቅ የተቆለመመ ፕሮፋይል አልደረሰኝም ይልሃል:: መረጃ አሞላል በጽሑፍም በቪዲዮም ልከህለት የማይሰማ ብዛቱ::
ከቴሌብር ወይም ሌላ ባንክ ብር የላከ
ሀብታሙ ወይም ኢሊያስ የሚባል ሰው ስምና አድራሻ ለመገመት
Habtamu
Habitamu
Habetamu
ሀብታሙ
ሃብታሙ
ሐብታሙ
ሓብታሙ
ኀብታሙ
ኃብታሙ
ኻብታሙ ሁላ ተጠቅመን ቻት ውስጥ አመላካች መረጃ እንፈልጋለን:: ከዚያ የሆነ ግሩፕ እንከተዋለን::
Elias
Elyas
Eliyas
Ilias
Iliyas
ኢሊያስ
ኤሊያስ እያልን መከራ ነው የምንበላው:: በተባለው ትእዛዝ መሠረት ቢሞላ የሰከንድ ሥራ ነው::
በዓብዱ የሚጀምርማ ተውት:: ገና ስናየው ይደክመናል::
👉🏼 ኮሜንት ላይ ግጥጥጥም አድርጎ ጽፎ ሄዶ መረጃ ልኬያለሁ የሚል ብዛቱ::
👉🏼 በፖስታ ቤት ካደረግነው በሗላ በፍጹም መጭበርበር የለም:: ስህተት ቢያጋጥም እንኳ የተሳሳትናቸውን ለማስተካከል so easy. እንዲሁም ከፍሎ የማይደርሰው አንድም ሰው አይኖርም:: የብር አታችመንት ቦታ የመጠጥ ኮዳ ፎቶ የላከ ሰው ሁላ አለ:: ቢሆንም ቢሆንም ከፍለህ አሳትመህ በየመጻሕፍት ቤቱ በዱቤ በትነህ በአምስት ዓመት ከመለቃቀም በጣኣኣኣኣኣም ይሻላል::
22
6August 30, 2026 3.1K 2