ሀብታም ያልሆንኩት ሕሊናዬን አልሸጥም ብዬ ነው ይልሃል:: ሲጀመር መሸጫ ቦታውን ታውቀዋለህ? ዋጋስ… — Hasen Injamo — TG.ME

ሀብታም ያልሆንኩት ሕሊናዬን አልሸጥም ብዬ ነው ይልሃል::

ሲጀመር መሸጫ ቦታውን ታውቀዋለህ? ዋጋስ ያወጣልሃል? ሕሊናህ ምን ይዟል? ንብረት አፍርቷል? ዝና አምጥቷል? ማን ባዶ ሕሊና ይገዛል? አንተ እራሱ ከ7 ዘ^ር የተዋረሰ እከክ ያለበትን ሕሊና ትገዛ ነበር?

አዎ ሕሊናቸውን የማይሸጡ አሉ:: ግን ሀብታም ሆነው የማይኮሩና በምጽዋት የበረቱ, ትልቅ ሥልጣን ይዘው ኃላፊነት የሚሰማቸው, ታላቅ የኃይማኖት አባት ሆነው ከፈጣሪ ውጭ ማንንም የማይፈሩ ይኖራሉ:: ፀሓይን በቀኝ ጨረቃን በግራ ቢያኖሩላቸው ከዓላማቸው ፍንክች የማይሉ የታላቅ አዕምሮ ባለቤቶች አሉ:: ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ የሆነ ኑሮውን የሚቀይር አዕምሮ የሌለው ሰው ማንም አይገዛውም::

በቀላሉ ሲጠቃለል:- ሕሊናህን ገበያ ወስደህ አስገምተህ የሆነ አሪፍ ቢዝነስ ጋር ፊትለፊት ተጋፍጠህ ወይም ማንም በማያይህና በማይሰማህ ቦታ ላይ አሪፍ ዘ^ረፋ አግኝተህ "አይ አምላኬን እፈራለሁ" ብለህ ትተኸው አልፈሃል?
❤37😁16👍5🤔3
September 1, 2026 2.4K 8