ለመ-ገንዘብ መጽሐፍ ከፍለው የሪል ኢስቴት ጉዳይ የምንጠቀምበት ቴሌግራም ውስጥ የላኩ አሉ ወላሂ:: ሀጂ መጽሓፌን ይለኛል:: ዛሬ የሪል ኢስቴቱን ቴሌግራም ጎብኘት ሳደርግ እዚያ ልከዋል:: የሪል ኢስቴቱ እኮ ለብቻው ተዋቅሮ በራሱ ሠራተኞች እየሄደ ሲሆን የመጽሓፍ ጉዳይ አይመለከታቸውም:: ግን ፖስቱን ወደ ሗላ ሄዳችሁ ስትፈልጉ እንዴት የመ-ገንዘብን ቴሌግራም ሊንክ አላገኛችሁም?
ብቻ ያም ሆነ ይህ ከፍሎ መረጃ ልኮ ፖስታ ቤት ያልተላከለት አንድም ሰው የለም:: እዚህ መጥተህ አልደረሰኝም ከማለትህ በፊት ስም, ስልክ, አድራሻ አድርሰን:: በተለይ ከ Other bank ወደ ኢት ንግድ ባንክ የከፈላችሁ ሰዎች አይደለም አድራሻ ቀርቶ ስማችሁን አንድ ፊደል እንኳ ማግኘት በፍጹም አይቻልም:: በባንኩ ብራንች ደረጃ እንኳ ማግኘት አይቻልም:: ስለዚህ ብራችሁን ነው ቋጥረን የምናስቀምጠው::
6September 3, 2026 1.7K 1