ትላልቅ ማለትም ኮርፖሬት ድርጅቶችን ተቀጥረው የሚመሩ ወይም ከመሩ ሰዎች ይልቅ የሊስትሮ ሳጥን የመሩ ሰዎች የተሻለ በራስ መተማመን አላቸው:: ትልቅ ድርጅት የሚመሩ ሰዎች የማሽን አንድ ክፍል ወይም እንደ ስፔር ናቸው:: ለምን ክራንክሻፍት አይሆኑም:: በማንኛውም ተመሳሳይ ስፔር ይቀየራሉ:: ድንገት ቢባረሩ በራሳቸው ችለው ለመቆም ረጅም ስብራት እና ዝገት ማስተናገድ አለባቸው:: ጭንቅላታቸው ውስጥ ቅጥር ነው ያለው:: ወሬያቸው ደግሞ በጣም ገራሚ ቢሆንም በራስህ ችለህ ድርጅት አቋቁም ብትሉዋቸው ይነስራቸዋል:: ኮርፖሬት ድርጅት የሌለን ኮርፖሬት CEOዎች ከስክራች ተነስቶ እንዴት እንደሚያድግ ስነልቦና ስላላሳደጉ ጭምር ነው::
አንድ ምሳሌ ልጨምርላችሁ:: ከሦስቱ ብ^ሔሮች ውጭ ያለን ብሔ^ር ሀገር ምራ ብትለው አልቻልኩም ብሎ ጥሎ ይወጣል:: ከእነዚህ ውስጥ አንደኛውን ብንወስድ ይህንን ስነልቦና ለማዳበር ብዙ ማገዶ ፈጅቷል:: ግንሳ? ከአስር ዓመት በፊት የነበረውና አሁን ያለው ስነልቦናው አንድ አይደለም:: Part of ስትሆን እና whole ስትሆን ስነልቦናህ ይለያያል:: ከበሮ በሰው እና በራስ እጅ እንደሚለያየው ማለት ነው:: እያንዳንዱን የቤት ሥራ በቤት ውስጥ "አጋዥ ሠራተኛ" ያደገ ልጅ እና በ Hardship ውስጥ ወይም ተጋግዞ ሲሠራ ያደገ ልጅ እኩል ኃላፊነት አይሸከሙም:: ሞልቃቃዎቹ በወላጅ ውርስ ሲካሰሱ ይኖራሉ:: ሲበታተኑ ከአንድ ማኅጸን የወጡ አይመስሉም:: በእርግጥ ወላጅም ቀድሞ ማከፋፈል አለበት:: ልክ እንደዚሁ ተቀጥረው ትላልቅ ድርጅቶችን የመሩ ሰዎች ከወሬ የዘለለ ቁምነገር አታገኙባቸውም:: ምክንያቱም ቢዝነስ ከ scratch ተነስቶ እንዴት እንደሚያድግ አያውቁም::
ለሚስቶቻችን እንደ አባቷ የማንሆነው ... ወልደውና አሳድገው ትልቅዬ ከሆነች በሗላ ነው የምናውቃት:: እስቲ ሚስትህን ልብ በላት:: አባቷ ምን ያህል እንደለፉባት አስበኸው ታውቃለህ? ያ ሁሉ ልፋት አንተ አቅፈሃት እንድትተኛ ነው እንዴ? አባቷን ካባትህ ነጥለህ ማየት እንደሌለብህ ካወቅህ አንተ ተቀጣሪ ባል ሳትሆን አባት ነህ:: ካልሆነሳ? ሴት ልጅ ወልደህ አሳድገህ ለትዳር እስክታደርስ አይገባህም:: ቢዝነስም ላይ የሆነ ድርጅት ተቀጥሮ የኖረ ሰው ባል ነው እንጂ አባት አይደለም:: ወሬው ባላዊ እንጂ አባታዊ ሊሆን አይችልም:: የተቀጣሪነት እንጂ የአሳዳጊነት ስነልቦና experience አላደረገም:: ባል ሚስቱ ጋር ከተደባበሩ እመጭ ብሎ ፍንጥር ይላል:: ትእግስት የለውም:: አባት ግን ልጄ ደበረኝ ደበረችኝ ሊል አይችልም:: ገርፎም ቢሆን ያስተካክላል:: በግሉ ትንሽም ይሁን ድርጅትን ከስክራች አንስቶ ይዞ የሚሄድ ሰው ወሬ አያበዛም:: ተጣማሪ አጋዥ አይፈልግም:: የተግባር ሰው ነው:: የማሽን ጥርስ ወይም ስፔር ሳይሆን ሙሉ ማሽኑ ነው:: ለመንቀሳቀስ ነዳጅ ወይም ኤሌክትሪክ ብቻ ነው የሚፈልገው:: ተቀጣሪ የነበረው ግን ምን የማይፈልገው ነገር አለ?
44
11
4
1
1September 3, 2026 2.6K 11