የኮርፖሬቶክራሲ እና የAI ጋብቻ፡
አዲሱ የዓለም ሥልጣን ውህደት
===================
የትልልቅ ኮርፖሬሽኖች፣ የባንኮች እና የመንግሥታት ትስስር (Corporatocracy) ከዘመኑ ከፍተኛው የቴክኖሎጂ ምጥቀት (AI) ጋር ያደረጉት ስትራቴጂካዊ ጋብቻ የዓለምን የፋይናንስ እና የፖለቲካ ስርዓት በከፍተኛ ፍጥነት እየቀየረው ይገኛል።
የትስስሩ 4 ዋና ዋና ነጥቦች፡-
1. መረጃ እንደ አዲሱ ሀብት፦ የሰዎች ዕለታዊ እንቅስቃሴ እና የገንዘብ ዝውውር በሜታዳታ መልክ ይሰበስባል፤ AI ደግሞ ይህንን በመተንተን የሰዎችን ባህሪና ገበያ የመቆጣጠር አቅም ይሰጣቸዋል። ለመረጃ አሰባሰብ የስልኮቻችን ባትሪ የማይወልቁ በመሆናቸው በፊት እና የሗላ ካሜራ ጭምር መረጃ ይሰበሰባል:: ሜታዳታ ዋነኛ ኃይል ሆኗል::
2. የካፒታል እና የሞኖፖሊ ውህደት፦ የAI ልማት ግዙፍ ሀብት እና የመረጃ ማዕከላትን ስለሚጠይቅ፣ የሥልጣን እና የገንዘብ የበላይነቱ በጣት በሚቆጠሩ ግዙፍ ኩባንያዎች እጅ እየተከማቸ ነው።
3. ፕሮግራመብል የፋይናንስ ስርዓት (ቀጣይ ሂደት)፦ በማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ገንዘቦች (CBDCs) እና በAI ትስስር፣ የገንዘብ ፍሰት እና ህዝባዊ ወጪዎች በእውነተኛ ጊዜ (Real-time) የመከታተልና የመገደብ አቅም እየፈጠረ ነው።
4. የዲጂታል ፊውዳሊዝም ስጋት፦ ጥቂት የቴክኖሎጂ ባለቤቶች የዲጂታል ዓለም «ጌቶች» ሲሆኑ፣ ህብረተሰቡ ደግሞ መረጃ አምራች እና ተጠቃሚ ብቻ የሚሆንበት አደገኛ ስርዓት ሊፈጠር ይችላል።
የመፍትሔ አቅጣጫዎች፡
1. ትክክለኛ ትምህርት (Right Education)፦ የፋይናንስ ስርዓቱን፣ የመረጃ ፖለቲካን እና የቴክኖሎጂውን አካሄድ በትክክል መረዳት። (ሦስት ሲሆኑ በመ-ገንዘብ ተብራርተዋል)
2. እውነተኛ ንብረቶች (Real Assets)፦ በዲጂታል ቅዠት ላይ ብቻ ሳይሆን ተጨባጭ በሆኑ እውነተኛ ሀብቶች ላይ የተመሰረተ መሰረት መገንባት።
3. ያልማከሉ (Decentralized) አማራጮች፦ ክፍት (Open-source) የቴክኖሎጂ እና የፋይናንስ ሥርዓቶችን መጠቀም። የጓሮ አትክልት, vertical farming ማለትም ሽቅብ ግብርና መጥቀስ ይቻላል:: በዚህኛው አስተራረስ ሜዳ ሳይወረድ ቤትና ጓሮ ላይ ሽቅብ ይመረታል:: (ቢጃይ ናይከር በዚህ expert ይመስለኛል)::
እነዝህ አብዛኛዎቹ በመ-ገንዘብ 2 በተለይ 4ኛ እትም እና በታዳጊዎቹ እትም ተብራርተዋል::
7September 4, 2026 1K 1