Ai እንደሰው ሆኖ ፍርድ ቤት ሊያቆመን ይችላል:: ምክንያቱም ቀደም ብለን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር, አክሲዮን ማኅበር የሚባል አርተፊሻል ሰውነት ያላቸው ድርጅቶችን አቋቁመን እየኖርን ነው:: የአንዳችሁ PLC መክሰስ መከሰስ የሚያስችል ሕጋዊ ሰውነት አለ:: የሰው ሥራ አስኪያጅ እና የሰው ጠበቃ ቀጥሮ ሲያሠራ ኖሯል:: በቀጣይ ግን ጠበቃ አይፈልግም:: ሥራ አስኪያጅም Bot 🤖 ይቀጥራል:: ስለዚህ ሁለት አርተፊሻል ሥርዓቶች ጋር እንፋጠጣለን:: አሁን አዲስ የፋይናንስ ኢንስትሩመንት ላይ ጥናት እያካሄድኩ ነው:: ፊያት ሳይገባን ሜታዳታ ተተካ:: አሁን ደግሞ በአርተፊሻል ሥርዓቶች እየተወረርን ነው::
የቀድሞ ሥርዓቶች ከባድ ቢመስሉም በትንሽ መረጃ ብዙ ዕውቀት እናገኝ ነበር:: አሁን በብዙ መረጃ ትንሽ ዕውቀት ነው የምናገኘው:: ተምሮ ዶክተር የሆነ ሰውዬ የወጥ አቀቃቀል አያውቅም:: ብዙ ምሁራን ውጭ ሀገር ለዶክትሬት ተልከው ምግብ መቀቀል ስለማይችሉ አቋርጠው ይመለሳሉ:: በጎግልና በAi የታገዘ ስንትና ስንት መረጃ ታጥቀን እንኳ የምናውቀው ትንሽ ነው::
ለምን?
ቢዝነሱ አርተፊሻል ኮርፖሬሽኖችና አርተፊሻል የፋይናንስ ሥርዓቶች ወስደውታል:: ስለፋይናንስ ሥርዓት የሚያውቀው ሰው በጣም ጥቂት ነው:: ፊያት ምን እንደሆነ የማያውቅና እኔ በተደጋጋሚ ስጽፈው በቡድን የተከራከሩ ሰዎች ገጥመውኝ "ይህ ቃል ዐረብኛ ነው ወይ?" ብለውኛል:: ላቲንኛ እንደሆነ አስረድቼ ገላገልኳቸው:: የድህነቴ ብቸኛ ምንጭ የፋይናንስ ሲስተሙን አለመማሬ እንደሆነ ያወቅሁት ዘግይቼ ነው:: በፋይናንስ እስከ ማስተርስ ስማር ትምህርቱ ከድህነት እንዴት እንደምወጣ አላስተማረኝም:: የተማርኩት ለአርተፊሻል ኩባንያዎች ምርጥ አካውንታንትና ፋይናንሻል አናሊስት እንድሆን ነው:: ለዘርፉ ቅርብ የሆንኩ ሰው እንዲህ ድህነት ከተዘባበተብኝ ከዚያ የራቀ ሰው ለአርተፊሻል ሥርዓቱ ያለው ዕውቀት በጣም ኢምንት ነው:: ይህንን ሥርዓት ሌላ አርተፊሻል ሥርዓት ሊመራው ነው::
_____
ለቀጣይ ሦስት ዓመት ምንም ዓይነት መጽሓፍ እጽፋለሁ አላልኩም ነበር:: ሞትኩ እኮ:: ሲስተሙ ደግሞ ይብስ እየገዛን ነው:: ትንሽ ልሸቅልና እጽፋለሁ::
13
4
1
1September 4, 2026 1.6K 1