ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨ ❴Part 267❵ #hadith267 "ጃቢር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፡- እሳቸው… — 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 — TG.ME

𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨ ❴Part 266❵ #hadith266 "ሐኪም ኢብኑ ሒዛም ረ.ዐ እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል በአንድ ወቅት የአላህ መልእክተኛ ሰ.ዕ.ወ የሆነ ነገር ጠየኳቸው ሰጡኝ ደግሜ ጠየኳቸው ሰጡኝ እንደገናጠየኳቸው አሁንም ሰጡኝ ከዚያም እንዲህ አሉሐኪም ሆይ ይህ ገንዘብ ጣፋጭ እና አረንጓዴ ነው ቸርበሆነች ነፍስ የያዘው ሰው በረካ ይሆንለታል…
ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ

❴Part 267❵ #hadith267


"ጃቢር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፡- እሳቸው (ጃቢር)ከአሏህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ጋር ወደ "ነጅድ" አቅጣጫዘመቱ፡፡ መልዕክተኛው (ሶ.ዐ.ወ) ከዘመቻ ሲመለሱእሾሃማ ከሆነ ሸለቆ አካባቢ ሲደርሱ የእኩለ ቀን የእረፍትሰዓት (ቀይሉላ) ደረሰባቸው፡፡ እዚሁ ስፍራ ላይ ሰፈሩ፡፡ሰዎች በየዛፎቹ ጥላ ስር ተጠለሉ፡፡ የአሏህ መልዕክተኛ(ሶ.ዐ.ወ) ከአንድ እሾሃማ ዛፍ ጥላ ስር አረፉ፥ ጦራቸውንከዛፉ ላይ አንጠልጥለው፡፡ እንቅልፍ አሸለበን፡፡ ብዙምሳይቆይ የአሏህ መልዕክተኛ ጠሩን፡፡ አንድ"አዕራቢይ" (ገጠሬ) ከጎናቸው አለ፡፡ "ይህ ሰው ተኝቼእያለሁ በኔ ላይ ጎራዴ መዘዘ፡፡ ሾተን ከአፎቱ መዞ አየሁት፡፡"ከእኔ ማን ያድንሃል?" አለኝ፡፡ "አሏህ" አልኩት ሶስትጊዜ፡፡" ካሉ በኋላ ተቀመጡ፡፡ አልተቆጡትም፡፡

(ቡኻሪናሙስሊም ዘግበውታል)

በሌላ ዘገባ ደግሞ ጃቢር እንዲህ ሲሉ ማስተላለፋቸውተወስቷል፡-• "ዛተ አር-ሪቃዕ" በተባለ ዘመቻ ወቅት ከአሏህመልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ጋር ነበርን፡፡ ጥላማ ከሆነ ዛፍደረስን፡፡ ለአሏህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ተውንላቸው።አንድ አጋሪ ሰውዬ መጣ፡፡ የአሏህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ)ጎራዴ ከዛፉ ላይ ተንጠልጥሏል፡፡ ጎራዴውን በመልዕክተኛው ላይ አነጣጠረና፡- "ትፈራኛለህ?"አላቸው፡፡ "አልፈራህም" ሲሉ መለሱለት፡፡ "ከኔ ማን ያድንሃል?" አላቸው። "አሏህ" አሉ፡፡

አቡበክር ኢስማዒል ባስተላለፉት ሶሒሕ ዘገባ ደግሞ፡-"ከኔ ማን ያድንሃል?" አላቸው፡፡ "አሏህ" አሏት፡፡ ጎራዴውከእጁ ወደቀ። የአሏህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ጎራዴውንያዙና፡- "ከኔ ማን ያድንሃል?" አሉት፡፡ "ክፉን በክፉ የማይመልስ ደግ ወዳጅ ሁን" አላቸው፡፡ "ከአሏህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንና እኔ የአሏህ መልዕክተኛ መሆኔን ትመሰክራለህን?" አሉት፡፡ "ይህንን አልፈፅምም፡፡ ግናካንተ ጋር ላልዋጋና አንተን ከሚወጉህ ሰዎች ጋር ላላብርቃል እገባለሁ" አላቸው፡፡ ከባልደረቦቹ ዘንድ ሄደና፡-"ከሰው ሁሉ ይበልጥ ደግ ከሆነ ሰው ዘንድ ነበርኩ"አላቸው፡፡

( ቡኸሪ ዘግቦታ )



📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/17616

🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
🥰5❤3🍓1
August 5, 2026 2.1K 1 2