ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨ ❴Part 266❵ #hadith266 "ሐኪም ኢብኑ ሒዛም ረ.ዐ እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል… — 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 — TG.ME

𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨ ❴Part 265❵ #hadith265 "ኢብኑ ኡብባስ (ረ አ) እንዲህ ሲሉ አስፍረዋል ።ሀስቡን አላህ ወኒእመል ወኪል አላህ በቂያችን ነው በእርሱ መመካት ምን አማረ የሚለው ቃል ነብዮ ኢብራሂም ( አ ሰ) እሳት ውስጥ የተጣሉ እለት ብለውታል ። ነብዮ መሀመድ (ሰ አ ወ) ሰዎች ጦር አከማችተውላችኋልና ፍርዋቸው ባሏቸው ጊዜ ሁኔታውን ኢብኑ አብባስን (ረ አ) ጠቅሰው በኻሪ ባሰፈሩት…
ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ

❴Part 266❵ #hadith266


"ሐኪም ኢብኑ ሒዛም ረ.ዐ እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል በአንድ ወቅት የአላህ መልእክተኛ ሰ.ዕ.ወ የሆነ ነገር ጠየኳቸው ሰጡኝ ደግሜ ጠየኳቸው ሰጡኝ እንደገናጠየኳቸው አሁንም ሰጡኝ ከዚያም እንዲህ አሉሐኪም ሆይ ይህ ገንዘብ ጣፋጭ እና አረንጓዴ ነው ቸርበሆነች ነፍስ የያዘው ሰው በረካ ይሆንለታል በጉጉትና በስስት የያዘ ደግሞ በረከትን ያጣበታል እየበላ እንደማይጠግብ ይሆናል. ከላይ የምትሆን ሰጭ እጅ በታች.ከምትሆን (ከተቀባይዋ) እጅ በላጭ ናት። ሐኪም ትረካቸውን በመቀጠል እንዲህ አሉ። የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በዚያ በእውነት በላክዎ አምላክ እምላለሁ! ከእንግዲህ ይኽችን ዓለም በሞት እስክለያት ድረስ ከርሶበኋላ ማንንም ምንም ነገር ላለመለመን ወስኛለሁ አቡበክር ሐኪምን አንዳች ነገር ሊሰጧቸው ይጠሩዋቸውነበር። ሐኪም ግን ከአቡበክር ምንም ነገር መቀበልን አይፈቅዱም ከዚያም ዑመር ሊሰጡዋቸው ጠሯቸውእርሳቸው ግን ሊቀበሏቸው አልፈቀዱም። (ዑመርም) እንዲህ አሉ። ሙስሊሞች ሆይ! በሐኪም ጉዳይ ምስክሬሁኑ። አላህ ከዚህ የምርኮ ገንዘብ የመደበለትን ድርሻውን ሰጥቼው ለመቀበል አልፈቅድ ብሏል። ሐኪም እስከሞቱበት ዕለት ድረስ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)በኋላ ማንንም ለምነው አያውቁም።

(ቡኻሪ ሙስሊም)



📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/17597

🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
❤5🥰5
August 4, 2026 2.1K 2