አንብቡት ይጠቅማችኋል
አንድ ልጅ እናቱን በጣም ይጠላት ነበር። ለምን ቢባል እናቱ አንድ አይኗ የለም ነበር። "የአንድ አይን ባለቤት ልጅ" እየተባለ በትምህርት ቤት ስለሚሳለቁበት፣ እናቱ ወደ ትምህርት ቤት ስትመጣበት ይሸማቀቅና ይቆጣ ነበር። "ለምንድነው እንዲህ ሆነሽ የምታሳፍሪኝ? ብትሞቺ ይሻል ነበር!" ብሎ ይጮህባት ነበር።
ልጁ አድጎ፣ ተምሮና ሀብታም ሆኖ ትልቅ ከተማ ውስጥ መኖር ጀመረ። ትዳር ይዞ ልጆች ወለደ። አንድ ቀን እናቱ ልጇን ናፍቃ ልትጠይቀው ቤቱ መጣች። ልጆቹ ግን አያታቸውን አይተው ደነገጡ፤ እርሱም "ለምን መጥተሽ ልጆቼን ታስፈራሪያለሽ? ውጪልኝ!" ብሎ አባረራት።
ከወራት በኋላ እናቱ መሞቷን ሰማ። ወደ ቤቷ ሲሄድ እናቱ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ትታለት ነበር፦ "ልጄ ሆይ፣ ሁልጊዜ ስላሳፈርኩህ ይቅርታ። ግን አንድ ሚስጥር ልንገርህ... ትንሽ ህፃን ሳለህ አደጋ ደርሶብህ አንድ አይንህን አጥተህ ነበር። እኔ ግን ልጄ በአንድ አይን እንዲያድግ ስላልፈለኩ፣ የራሴን አንድ አይን አውጥቼ ሰጠሁህ። ዛሬ አንተ በአይኔ እያየህ ስላለህ እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ።"
በአለም ላይ ትልቁ ስቃይ ለአንድ ሰው ሙሉ ህይወትህን ሰጥተህ፣ ያ ሰው ግን እንደ ውርደት ሲቆጥርህ ነው። እናትና አባት የሰጡንን ብርሃን ረስተን፣ በራሳችን ብርሃን የፈጠርን ይመስለንና ስንኮራ ነፍሳችን በቁም ትሞታለች።
ማንም እንደ ወላጆችህ ሊወድህ መስእዋትነት ሊከፍልልህ አይችልም
29
8
5
2September 3, 2026 512 5 6