✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨
❴Part 255❵ #hadith255
"ኡመር ኢብን አል ከጧብ(ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉአስተላልፈዋል ከእለታት አንድ ቀን ከአላህ መልዕክተኛ (ሶአ ወ) ዘንድ ተቀምጠን እያለን አንድ በጣም ነጭ የሆነልብስ የለበሰ ጸጉሩ በጣም ጥቁር የሆነ የጉዞ ምልክትየማይታይበት ከመካከላችንም ማንንም የማያውቅየማያውቀው አንድ ሰው ብቅ አላ ጉልበቱን ከነብዩሙሀመድ (ሶ ዐ ወ)ጉልበት ጋር አሳብቶ ተቀመጠመዳፎቹን ደግሞ ታፋዎቹ ላይ አደረገ ሙሀመድ ሆይ! ስለእስላም ንገረኝ ሲል ጠየቀ "ኢስላም ከአላህ ሌላ የሌላመሆኑን እና ሙሀመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውንመመስከር ሶላትን አስተካክለህ መስገድ ዘካን መስጠትየረመዷንን ጾም መፆምትህና ወደ ሀጅ ለመጓዝ ችሎታውያለህ ከሆነ ሀጅ ማድረግ ነው " ሲሉ የአላህ መልእክተኛ(ሶ. ዐ .ወ) መለሱለት " እውን ብለዋል አላቸው" ገረማንይጠይቃቸዋል እውን መናገራቸውን ይናዘዛል "ስለ ኢማን( እምነት ) ይንገሩኝ አላቸው "በአላህ፣ በመላዕክት፣በመጻህፍት፣ በመልዕክተኞች በዕለተ ትንሳኤና ክፉም ሆነበጎ በአላህ ዕቅድ እና ህግ ማመን ነው " አሉ "ስለኢህሳን ይንገሩኝ " አላቸው አላህን እንደምታየው አድርገህማምለክህ ነው፣ አንተ ባታየው እርሱ ያይሀል" አሉት፡፡ "ስለ ፍርዱ ቀንንገሩኝ" አላቸው፡፡ "የሚጠየቀው ሰው ከጠያቂው የበለጠእውቀት የለውም" ሲሉ መለሱለት፡፡ "እሺ ስለ ምልክቶቿንገሩኝ" አለ፡፡ "የሴት ባሪያ እመቤቷውን ትወልዳለች፡፡ጫማ የሌላቸው፥ የታረዙ፥ ድሆችና ፍየል እረኞች (የነበሩሰዎች) ታላላቅ ሕንፃዎችን በመገንባት ሲፎካከሩትመለከታለህ" አሉት። ከዚያ ወጥቶ ሄደ፡፡ ትንሽ ቆየሁ፡፡"ዑመር ሆይ! ጠያቂው ማን እንደሆነ አወቅከውን?" አሉኝመልዕክተኛው (ሶ.ዐ.ወ)፡፡ "አሏህና መልዕክተኛውያውቃሉ" አልኩ፡፡ "ጅብሪል ነው፡፡ ሃይማኖታችሁንሊያስተምራችሁ ከናንተ ዘንድ መጥቶ ነው" አሉ፡፡
(ሙስሊም ዘግበውታል)
📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/17441
🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
20
2
1July 23, 2026 2.4K 4