በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ80 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን በአዳሪ ትምህርት ቤቶች ለመቀበል… — Gambella Educational Media — TG.ME

በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ80 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን በአዳሪ ትምህርት ቤቶች ለመቀበል ምዝገባ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች የተማሪ ምዝገባን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የሚኒስትሩ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክንድዬ ገብረሕይወት (ፕ/ር)፤ በ8ኛ ክፍል ከ80 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን በማወዳደር ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን፤ ከገጠራማ እና ከአርብቶ አደር አካባቢዎች ለሚመጡ ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ምዝገባው በሚኒስቴሩ በይነ-መረብ በኩል ያለምንም ክፍያ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ውጤታቸውን በፒዲኤፍ (PDF) ስካን በማድረግና የፈተና መለያ (ID) ቁጥራቸውን በመጠቀም ባሉበት ሆነው በመመዝገብ ወደ አዲስ አበባ ሳይመጡ ባሉበት ክልል ሆነው በበይነ-መረብ ፈተናውን ይወስዳሉ ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአምስት አካባቢዎች (ጂጂጋ፣ ጋምቤላ፣ ቦንጋ፣ ቡኢ እና ወሊሶ) አገልግሎት እየሰጡ ካሉት አራት አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ማለትም በባህር ዳር፣ አርባ ምንጭ፣ ድሬደዋና አሶሳ መቀበል እንደሚጀምሩ ጠቁመዋል፡፡ በሁሉም ክልሎች የተገነቡ 13 የፌደራል አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ፣ እያንዳንዱ አዳሪ ትምህርት ቤት እስከ 1,000 ተማሪዎችን በመቀበል በየዓመቱ 13 ሺህ አዳዲስ ተማሪዎችን የማስተናገድ አቅም ይኖራቸዋል ሲሉ ተናግረዋል። ለትምህርት ቤቶቹ የሚያስፈልጉ ዳይሬክተሮችና መምህራንም በፌደራል ደረጃ በልዩ ሁኔታ ተመርጠው እየተቀጠሩ ይገኛሉ ሲሉ ሙሉ መረጃ ይመልከቱ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.facebook.com/61555466904217/posts/pfbid0NpoYbu7VjLcvYxXxnKTxQn964cyZnfXrfYD8CrGeGzLn7LWFmwgX5zPJJ2TMzhv3l/

August 20, 2026 2.6K 10