በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በክልል አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ትምህርት… — Gambella Educational Media — TG.ME

በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በክልል አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ተደርጓል። የቢሮው ኃላፊ አቶ ኡኩኝ ኡኬሎ እንዳሉት ክልል አቀፉን ፈተና አስመልክተው እንደለጹት በክልሉ በ2018 የትምህርት ዘመን በ6ኛ ሆነ 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል። በክልሉ የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል 84.08 ከመቶ ወደ ቀጣዩ የትምህርት ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት አስመዝግበዋል ብለዋል። በትምህርት ዘመኑ የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከወሰዱት 14 ሺህ 246 ተማሪዎች መካከል 11 ሺህ 978 ተማሪዎች 50 እና ከዚያ በላይ ማምጣታቸውን ገልጸዋል። እንዲሁም ባለፈው ሳምንት ይፋ በሆነው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል78.56 ከመቶ ወደ ቀጣዩ የትምህርት ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት ማጣቸውን ተናግረዋል። በትምህርት ዘመኑ በ6ኛና በ8ኛ ከፍል የተመዘገበው ውጤት ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ6ኛ ክፍል በ7.79 ከመቶ በ8ኛ ከፍል ደግሞ በ10 ከመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን ገልጸዋል። በትምህርት ዘመኑ የተሻለ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው የትምህርት ግብዓት ጨምሮ ሌሎች የትህምርት ማሻሻያና ሪፎርም ስራዎች በመከናወናቸው ነው ብለዋል። በዛሬው ዕለት ይፋ የሆነው የ6ኛ ከፍል ፈተናን https://gambella6.ministry.et በሚለው ገብቶ ማየት ይቻለል

August 20, 2026 2.6K 17