አርሰናል ከቼልሲ - የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 01፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ3ኛ ሳምንት… — FMC Sport ፋና ስፖርት — TG.ME

አርሰናል ከቼልሲ - የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 01፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ3ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል።

በዚህም ምሽት 12 ሰዓት 30 ላይ አርሰናል በሜዳው ኢምሬትስ ቼልሲን ያስተናግዳል፡፡

የሊጉን የዋንጫ ቅድመ ግምት አግኝቶ የውድድር ዓመቱን የጀመረው አርሰናል በሊጉ ያደረጋቸውን ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፉ ይታወሳል።

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት መድፈኞቹ በሊጉ ሦስተኛ ተከታታይ ድላቸውን ለማሳካት ወደ ሜዳ የሚገቡ ይሆናል።

በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ እየተመራ የውድድር ዓመቱን የጀመረው ቼልሲ በሊጉ ተከታታይ 3ኛ ድሉን ለማሳካት እያለመ ወደ ኢምሬትስ ያቀናል፡፡

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንደ ተጋጣሚው አርሰናል ሁሉ በሊጉ ያደረጋቸውን ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል ማድረጉ አይዘነጋም፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በሁሉም ውድድር እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አርሰናል አራቱን በማሸነፍ የበላይነት አለው።

በቀሪው አንድ ጨዋታ ደግሞ አቻ መለያየታቸው የሚታወስ ነው።

ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ ቀን 10 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ኤቨርተንን ይገጥማል።

https://www.facebook.com/share/p/199HoiXvV6/?mibextid=wwXIfr
👍3
September 6, 2026 1.1K 1