ኒውካስል ዩናይትድ እና ቦርንማውዝ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኒውካስል ዩናይትድ እና ቦርንማውዝ 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡
ቀን 8 ሰዓት 30 ላይ በተደረገው ጨዋታ የኒውካስል ዩናይትድን ግቦች ባርንስ እና ራምሴ አስቆጥረዋል፡፡
የቦርንማውዝን ግቦች ደግሞ ታቨርነር እና ቲያው በራሱ ግብ ላይ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የሊጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከኮቨንትሪ ሲቲ፣ ብሬንትፎርድ ከሰንደርላንድ፣ ብራይተን ከ ሊድስ ዩናትድ እንዲሁም ፉልሃም ከክሪስታል ፓላስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ሃል ሲቲ ከ አስቶንቪላ የሚገናኙ ይሆናል፡፡

September 5, 2026 1.3K 1