ሊቨርፑል የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል አሳካ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሊቨርፑል ኢፕስዊች ታውንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች አሌክሳንደር አይሳክ በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥሯል።
በጨዋታው ኮዲ ጋክፖ ሁለቱንም ለግብ የሚሆኑ ኳሶች አመቻችቶ ያቀበለው ተጫዋች ነው።
ከሁለት ተከታታይ የአቻ ውጤት በኋላ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድሉን ያሳካው ሊቨርፑል ነጥቡን ወደ አምስት ከፍ አድርጓል።
ተጋጣሚው ኢፕስዊች ታውን በበኩሉ ተከታታይ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
3September 4, 2026 902 1


