በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሴቶች ብቻ የካራቴ ውድድር ተካሄደ አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም… — FMC Sport ፋና ስፖርት — TG.ME

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሴቶች ብቻ የካራቴ ውድድር ተካሄደ
 
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጄ.ኪ.ኤስ ኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የመጀመሪያው የሴቶች ብቻ የካራቴ ውድድር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
 
በዚሁ ወቅት የጄ.ኪ. ኤስ ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሰለሞን ዘውዱ እንዳሉት፤ ውድድሩ ፌዴሬሽኑ ከያዘው ሴት ስፖርተኞችን የማብቃት እቅድ አካል አንዱ ነው።
 
በውድድሩ ካዛና ክለብ በካታ ምድብ አንድ ወርቅ፣ አንድ ብር እና አንድ የነሀስ ሜዳልያዎችን በማግኘት የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል፡፡

በውድድሩ ካንኩ ዳይ ክለብ በአንድ ወርቅ እና አንድ ብር 2ኛ እንዲሁም ዊነር ክለብ በአንድ ወርቅ እና ሁለት ነሀስ ሜዳልያዎች 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የፋይት ውድድር 3 የወርቅ ሜዳልያዎችን የወሰደው ዊነር ክለብ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል።
 
በውድድሩ ከ8 ቡድኖች የተውጣጡ 56 ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል።

በዳዊት መሐሪ
September 3, 2026 1K 2