ሪቻርልሰን ከቶተንሃም ስብስብ ውጪ ሆነ አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብራዚላዊው የፊት… — FMC Sport ፋና ስፖርት — TG.ME

ሪቻርልሰን ከቶተንሃም ስብስብ ውጪ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሪቻርልሰን ከቶተንሃም ሆትስፐር ስብስብ ውጪ ሆኗል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ በቅርቡ ሪቻርልሰን ክለቡን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረቡን መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

የ29 ዓመቱ ተጫዋች በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ስሙ ከኤቨርተንን ጋር ሲያያዝ ቆይቷል።

ሪቻርልሰን ለቶተንሃም ሆትስፐር 103 ጨዋታዎችን አድርጎ 27 ግቦችን አስቆጥሯል።

የተጫዋቹ ቀጣይ ማረፊያ የት ይሆናል የሚለው ይጠበቃል።
September 3, 2026 2K 1