ቶተንሃም ሆትስፐር ሙድሪክን ከቼልሲ አስፈረመ አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቶተንሃም… — FMC Sport ፋና ስፖርት — TG.ME

ቶተንሃም ሆትስፐር ሙድሪክን ከቼልሲ አስፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቶተንሃም ሆትስፐር ዩክሬናዊውን ተጫዋች ሙድሪክን ከቼልሲ አስፈርሟል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ሆትስፐር ተጫዋቹን ወደ ስብስቡ የቀላቀለው በውሰት ውል ነው።

የ25 ዓመቱ ተጫዋች በውሰት ውሉ መሰረት ለአንድ የውድድር ዓመት ያህል በሰሜን ለንደኑ ክለብ የሚቆይ ይሆናል።

ሙድሪክ በፈረንጆቹ 2023 ቼልሲን በ70 ሚሊየን ዩሮ መቀላቀሉ ይታወሳል።

ቶተንሃም ሆትሰፐር በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሳንድሮ ቶናሊ፣ ማቲያስ ፈርናንዴዝ፣ ሳቪኒሆ፣ ሮበርትሰን እና ኦማር ማርሙሽን የመሳሰሉ ተጫዋቾችን ማስፈረሙ ይታወሳል።

በአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢ የሚመራው ቶተንሃም ሆትስፐር በሊጉ ያደረጋቸውን ተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች መሸነፉ አይዘነጋም።
September 1, 2026 257 1