ሊቨርፑል ባርኮላን ከፒኤስጂ አስፈረመ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሊቨርፑል ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ብራድሊ ባርኮላን ከፒኤስጂ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
ፈረንሳዊው ተጫዋች በመርሲሳይዱ ክለብ ለአምስት ዓመታት የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል፡፡
ሊቨርፑል ለዝውውሩ 125 ሚሊየን ዩሮ ክፍያ የፈጸመ ሲሆን፤ የተጫዋቹ ብቃት እየታየ ደግሞ ተጨማሪ 20 ሚሊየን ዩሮ ክፍያ የሚከፍል ይሆናል።
የ23 ዓመቱ ተጫዋች በፒኤስጂ በነበረው ቆይታ 153 ጨዋታዎችን አድርጎ 39 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
በሌላ በኩል ማንቼስተር ሲቲ ብራዚላዊውን የመስመር ተጫዋች አላን ኤሊያስን ከፓልሜራስ አስፈርሟል፡፡
አላን በማንቼስተር ሲቲ ቤት ለአምስት ዓመታት የሚያቆውን ውል መፈራረሙ ነው የተገለጸው፡፡
ማንቼስተር ሲቲ ለ22 ዓመቱ ተጫዋች 40 ሚሊየን ዩሮ የዝውውር ሂሳብ ወጪ አድርጓል፡፡
አላን ለፓልሜራስ ባደረጋቸው 96 ጨዋታዎች 9 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ኤሊዮት አንደርሰን፣ እና አዩብ ቡአዲን ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡
August 31, 2026 1.9K 1

