አስቶንቪላ እና ሃል ሲቲ አቻ ተለያዩ አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አስቶንቪላ እና ሃል ሲቲ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ በተደረገው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ጨዋታቸውን አጠናቅቀዋል፡፡ አስቀድሞ በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ ኮቨንትሪ ሲቲን 1 ለ 0 እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ፉልሃምን 3 ለ 2 አሸንፈዋል፡፡ ሊድስ ከብራይተን እንዲሁም ብሬንትፎርድ ከሰንደርላንድ በተመሳሳይ 1 አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ ቶተንሃም ሆትስፐር ከኖቲንግሃም ፎረስት ያለምንም ግብ አቻ ሲለያይ ፤ ኒውካስል ዩናይትድ ከቦርንማውዝ 2 አቻ መለያየታቸው ይታወቃል፡፡
September 5, 2026 1.1K 1