ይቅር በለን
( በእውቀቱ ስዩም)
የዘራም አጨደ
ያጨደም አስገባ
ያስገባም ጋገረ
የጋገረም በላ"
ከዚያ ምን ይመጣል
ፍርፍር ሆኖ ገብቶ: ፍግ ሁኖ ይወጣል::
በሸመታም ይሁን: በወራሪ ዝርፍያ
በስርአት ይሁን : በሽምያ በግፍያ
በግብዣም ይድረሰን: ወይ በመቀላወጥ
የምንበላው ህብስት: የምንጨልፈው ወጥ
ማለፍያው ሰርገኛው: ዶሮና ምስሩ
ወደታች ስንምሰው : ብዝበዛ ነው ስሩ::
የርግማኑን ራስ : ሆድ ይዘን ተፈጥረን
መቸገር ሳያንሰን
ለጠበቃ አልባዎች ሸክም አሸጋግረን
ከጥንት እስከዛሬ
ጭንቅህን በልሳን ተርጉመህ ባትነግረን
ይቅር በለን በሬ
አህያ ሆይ ማረን!!

11July 1, 2026 1.4K 1 3