ብዙ ግዜ አያቴ ጋር ቁጭ ብዬ የምትነግረኝ እሰማት ነበር ።
አንድ ቀን ማታ ቁጭ ብለን ሰለነጌ መጨነቀን እያወራን ነብር ። ከማሃል አያቴ ስሙ ልጆች ስትል ቀጠለች ። ንጉሱ የሆነችን ሴት ነጌ ጣዋት ሁለት አንገት ያለው ፈረስ ካላመጣሽ ከነ ቤተሰብሽ እስራት ነው የማስተላለፍባችሁ ይላታል ። ሴትዮዋ ጨነቃት ጠበባት እናም ወደ ጎረቢት ሄዳ ትቀመጣለች ትነሳለች ግራ የተጋቡት ጎረቢቶቿ ምን ሆነሻል ሲሉ ጠየቋት ? ንጉሱ ያላትን ነገር ነገረቻቸው አንዱ ሰውዬ እና ለዚ ነው የምትጨነቂው አላት? አዎ አለች ። ሰውዬው አይዞሽ ለሊቱን ወይ ሁለት አንገት ያለው ፈረስ ተወልዶ ያድራል ወይ ንጉሱ ይሞታሉ ዝም ብለሽ ተኚ አላት ። ሲነጋ ንጉሱ ሞቱ ተበለ ። አያችሁ ነጌን አቅዱ እንጂ አትጨነቁ አለቺን አያቴ ።
t.me/fikee21
1June 29, 2026 1.2K 1 4