ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል: post #414 — TG.ME

እድሜ ለበደልሽ
እድሜ ለጭካኔሽ
እድሜ ላንቺ ክፋት
ላንቺ ይብላኝ እንጂ...
እኔማ.....
እንደ ምንም  ብዬ ያቺን ቀን አለፍኳት ።

እድሜ ላንቺ እድሜ ኑሪ ነፍ አመት
ማድመጥ ጀምሪያለሁ የእራሴን ልብ ምት
ምንድን ነው ትዝታ ምን ያደርጋል ናፍቆት
ምን ያደርጋል ትላንት
ምን ያደርጋል ፀፀት ላለፈ እንደ ዘበት ።

እና
ወደ አሻሽ ሂጂ
ያሻሽን አፍቅሪ ያሻሽን ውደጂ
ከኔ የተሻለ ሰው አግኝተሽ  እንደሁ
ይቅናሽ ብዬሻለሁ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /


t.me/fikee21
❤2
June 28, 2026 1.4K 4 1