ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች: post #449 — TG.ME

#ከህይወቴ ተምሬያለው
💥. አንዳንድ ሰው እንዲያፈቅራችሁ ማድረግ እንደማይቻል ተምሬያለሁ ፤ ማድረግ የሚቻለው ጥሩ አፍቃሪ መሆን ብቻ ነው ።

💥.ብስለት የሚመጣው ከሚያጋጥሙን ተሞክሮዎች ዓይነትና ከተሞክሮዎቹ ከቀሰምናቸው ትምህርቶች እንጅ ካከበርናቸው የልደት በዓሎች ብዛት እንዳልሆነ ተምሬያለሁ ።

💥.እንዳንዴ የቱንም ያህል ለሌሎች ብጨነቅ እና ግድ ብሰጥ አንዳንዴ አንዳንዶች በመልሱ ግድ ላይሰጡ እንደሚችሉ ተምሬያለሁ ።

💥.ጓደኞች ምንም ያህል ጥሩ ቢሆን አልፎ አልፎ ማስቀየማቸው እንደማይቀር ተምሬያለሁ ። ባስቀየምናቸው ሰዎች ይቅር መባል በቂ ያለመሆኑንና ራስንም ይቅር ማለትም እንደሚያስፈልግ ተምርያለሁ ።

💥.መታመንን ለመግንባት ዘመናት እንደሚያስፈልግ ፤ ለማውደም ግን ሰከንዶች ብቻ እንደሚበቁ ተምሬያለሁ ።

💥.አንዳንድ ጊዜ ተንሸራትተህ ስትወድቅ ይረጋግጡኛል ብለህ የምትጠብቃቸውና የምትፈራቸው ሰዎች ብድግ አድርግው በማንሳት እንደሚያስገርሙህ ተምሬያለሁ ።

💥.እውነተኛ ጓደኝነት እንደዚህም እውነተኛ ፍቅር በቦታ ርቀት ሳይግደብ ማበብ መፍካቱ እንደማይቆም ተምሬያለሁ ።

💥.በአስተዋይነት "እምቢ" ማለት ሁልጊዜም የንፉግነት ምልክት ያለመሆኑን “እሺ” ማለትም ሁልጊዜ ምግባረ ሰናይነትን እንደማያሳይ ተገንዝቢያለሁ ።

💥.ራስን ከጥፋተኝነት ስሜት እንዲሁም ከጥላቻ የምንገላገልበት ብቸኛ መንገድም የአለፈውን ጊዜ ረስተን ከአሁን ጋር እርቅ ማድረግ ስንጀምር እንደሆነ ተምርያለው ።
October 7, 2021 28.4K 160