በአንድ ዘመን ሀገረ-ህንድን የሚመራ ንጉስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ይሾማል።በወቅቱ የሀገሪቷን የደህንነት ጉዳይ ለሌሎች ሀገሮች መረጃ መስጠት በሞት ያስቀጣ ነበር።ታድያ የተመረጠው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር በዚህ ወንጀል ይያዝና ሞት ይፈረድበታል።ቅጣቱ የሚፈፀምበት ቦታ በሰዋራ ስፍራ የሚገኝ አዳራሽ ውስጥ ነበር።ታዛቢዎች አዳራሹን ሞሉ።ሁለት የመሞቻ መንገድ ለወንጀለኛው ቀረበ።በቀኝ በኩል አንድ የጥንት ጠብ-መንጃ(ጠመንጃ)፣በግራ:- ጥቁር ቀለም የተቀባ የተዘጋ በር ይገኛል።የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ የተዘጋውን በር ከፍቶ ለመግባትና ባልታወቀ የአሟሟት ሁኔታ ለመሞት ስላልደፈረ በጠመንጃ መሞትን መርጦ ተገደለ። ከንጉሱና ከንግስቷ በስተቀርም ሁሉም አዳራሹን ለቆ ሄደ። ንግስቷም ከጥቁሩ በር ጀርባ ስላለው የመግደያ አይነት ንጉሱን አጥብቃ ጠየቀች።ንጉሱም እንዲህ አለ"ከጥንት ጀምሮ ጠመንጃውም በሩም አለ ግን አንድም ተቀጪ በሩን አልመረጠም።ሁሉም የማያውቁትን ለማወቅ አልደፈሩም።ነይ ላሳይሽ"ይልና በሩን ከፈተ።ከበሩ በስተያ ልምላሜ ያለው ተራራ እንጂ ምንም አልነበረም።
/ህያውነት 1
/osho/ኦሾ
October 7, 2021 33.8K 95