" ......ተገቢውን ፍርድ ለመስጠት የምትሹ እናንተ ዳኞች ሆይ ...በስጋው ታማኝ ቢሆንም በመንፈስ ሌባ ለሆነ ሰው ምን ፍርድ ትሰጡታላችሁ ?......በስጋው ለሚያርድ በመንፈሱ ግን እርሱ ራሱ ለታረደውስ ምን ቅጣት ትጥሉበታላችሁ ?......እናስ በተግባር አታላይና ጨቋኝ ቢሆንም እርሱ ራሱ የተጨቆነውን የተዋረደውንስ እንደምን ትዳኙታላችሁ ?.....ገና ሳይፈረድባቸው ፀፀታቸው ከመጥፎ ድርጊታቸው በእጅጉ በልጦ የተገኘውንስ እንዴት አድርጋችሁ ነው ቅጣት የምትጥሉባቸው ?.......በአግባቡ እያገለገላችሁት የምትገኙት ያ ህግ በራሱ የሚሰጠው ፍትሀዊ ብይንስ ፀፀት አይደለምን ? እንደዚያም ሆኖ በንፁሃን ላይ ፀፀት ልታሳድሩ ወይም ከጥፋተኞች ልብ ላይ ፀፀት ነቅላችሁ ልታወጡ አይቻላችሁም ። ...." ገፅ ( 38 / 39 )
".....ወዳጆቼ ሆይ በእምነቶችና በባዶ ሐይማኖቶች ለተሞላች ሀገር እዘኑላት ....በጥባጮችን እንደ ጀግና በእልልታ ለምትቀበል ፣ አንፀባራቂ ድል አድራጊዎችን እንደ ለጋስ ለምታሞካሽ ሀገር እዘኑላት ..... መሪው ቀበሮ ፈላስፋው ቀጣፊ ጥበቡም መኮረጅና መለጣጠፍ ለሆነ ህዝብ እዘኑለት ..... አዋቂዎቿ በእድሜ መግፋት ዲዳ ለሆኑባት ፣ ብርቱ ልጆችዋ ገና ከህፃን አልጋ ላይ ላልተነሱላት ሀገር እዘኑላት ..... ግዛቷ ለተበጣጠሰባትና እያንዳንዱ ብጥስጣሽ ራሱን እንደ አንድ ሀገር ለሚቆጥርባት ሀገር እዘኑላት ..... ገፅ ( 153 )
የጠቢባን መንገድ
October 7, 2021 22.9K 34