•ንጉሱ በጣም ብርዳማ በሆነው ሌሊት ወደ ቤተመንግስቱ ሲገባ ስስ የሆነ ልብስ የለበሱ አንድ በእድሜ የገፉ የቤተመንግስቱን ጥበቃ ተመለከተ
.
ወደ እሳቸውም ተጠጋና አይበርዶትም? አላቸው
.
ሰውዬውም፦ይበርደኛል እንጂ ነገር ግን ብርድን የሚከላከል ልብስ የለኝም! አለ
.
ንጉሱ፦ወደ ህንጻው ከገባ በኋላ ከጠንካራው እና ብርድን የሚከላከል ከሱፍ የተሰራ ልብስ እንዲያመጣላቸው አንዱን አገልጋይ
ያዘዋል።
.
ጥበቃው፦በንጉሱ ቃል በጣም ተደሰቱ። ነገር ግን የንጉሱ አገልጋይ ረስቶት ሊያመጣላቸው አልቻለም።
.
ሌሊቱ ሲነጋ ግን ንጉሱ ከቤተመንግስቱ ሲወጣ ሰውዬው ሞተው ያያል።
.
አንድ ብጣሽ ወረቀትም በእጃቸው ይዘው ነበር ንጉሱን ወረቀቱም ማንበብ ጀመረ።
.
ደብዳቤውም እንዲህ ይላል
.
"ብርዳማ ሌሊቶችን መቋቋም እችል ነበር ነገር ግን ለኔ ብርድ የሚከላከል ልብስ #ቃል መግባትህ ሀይሌን ነጠቀኝ"
.
~~~~~~~ ~~~
ቃል የምትገባላቸው ሰዎች ቃልህን ከምታስበው በላይ ቦታ ሊሰጡት
ይችላሉና እናስታውስ ቃላችንን አንጠፍ።
October 7, 2021 22K 134