ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች: post #442 — TG.ME

አንድ ጊዜ ታላቁ ሸህ ኢብን ዐረቢ ወደ ደማስቆ ተራራ ይወጣና ማስተማር ይጀምራል፡፡ በመሃል "ሰዎች ሆይ! የምታመልኩት ጌታ ከእግሬ ሥር ይገኛል" አላቸው፡፡ ሰዎቹ በጣም ከመናደዳቸው የተነሳ አሰሩት፤ ሊገድሉትም ዝግጁ ሆኑ፡፡
ኢብን ዐረቢ ሥራዎቹ ጥቃት የተቀላቀሉበት ውዝግቦችን ከማስነሳታቸው የተነሳ ከሞተ በኀላ የተቀበረበት እንዳይገኝ ሃውልቱን ሁሉ አፈራርሰው ድራሹን አጠፉት፡፡
ታዲያ ኢብን ዐረቢ የሚታወቅባቸው በርካታ ንግግሮች አሉት፡፡ አንደኛው "ሲን ሺን ሲገባ ቀብሬ ይገኛል" የሚለው ዋናው ነው፡፡
ኢብን ዐረቢ ከሞተ ወደ ሶስት መቶ ዓመታት ሊሞላው ሲል ዘጠነኛው የዑስማንያ ኸሊፋ ሰሊም ሁለተኛው ደማስቆን 1516 ይማርካል፡፡ ሰሊም ከላይ የተጠቀሰውን የኢብን ዐረቢ ንግግር በወቅቱ ከነበረው ዓሊም ዘምቢሊ ዓሊ ኢፈንዲ ከነትንቢቱ ይሰማል፡፡ ሸኽ ዘምቢሊም የትንቢቱን ፍቺ ይነግሩታል- ሲን ማለት ሰሊም ወደ ሺን ማለት ሻም ሲገባ የሙሂይዲን ሐውልት ይሠራል።
ታዲያ ሰሊም ከከተማዋ የነገረ መለኮት ዓሊሞች ኢብን ዐረቢ "የምታመልኩት ጌታችሁ ከእግሬ ሥር ይገኛል" ብሎ የተናገረበትን ቦታ ጠይቆ ከተረዳ በኀላ ማስቆፈር ይጀምራል፡፡ የወርቅ ሳንቲሞች ክምር ያገኛል፡፡ ፃድቁ ኢብን ዐረቢ ምን ለማለት እንደፈለገ ይገልፃል፡፡ የወርቅ ሳንቲሞቹ ከተገኙበት ቦታ ብዙም ሳይርቅ የተቀበረበትን ቦታ ያገኘዋል፡፡ ሰሊም በተገኘው ወርቅ በቦታው ላይ መስጊድ እና የኢብን ዐረቢን ሐውልት ያሠራል፡፡
መስጊዱና ዶሪሁ አሁንም በደማስቆ ይገኛል፡፡ ሳሊሂያ ይባላል፡፡ ቃሲዩን ከሚባለው ተራራ ተዳፋቱ ላይ ነው፡፡ አሁን በአገሪቷ እየተካሄደ ባለው የእርስ በእርስ ጦርነትም ጉዳት አልደረሰበትም፡፡
አላህ ሆይ! በታላቁ ሸኽ ይሁንብህ፤ እባክህን ወዳንተ አቃርበን!
ቀደሰላህ ሲረሁ
October 6, 2021 19K 22