ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች: post #440 — TG.ME

ፈጣሪ እኛ እንጎበኛዋለን እንጂ እሱ አይጎበኘንም

እንድ የበቁ የዜን አባት አንድ ወጣት መጥቶ " ወደ ዜን መግቢያው በር በየት ነው ? " ብሎ ጠየቃቸው ። እሳቸው ግን መልስ ከመሰጠት በአርምሞ አለፉት። ልጁ በድጋሚ ጠየቃቸው ። አባ በዛን ሰአት እንዲህ ብለው ለወጣቱ ጥያቄን በጥያቄ መለሱለት ...
" ምንጩ ይሰማኸል ? "
ወጣቱ " የምን ምንጭ ? " ...ለደቂቃዎች የምንጩን ድምፅ ለማወቅ ትኩረት ሁሉ ወደእዚያው አደረገ ። የምንጩን ድምፅ ሲፈለግ በአእምሮ ሲንጡት የነበሩ ሀሳቦች ሁሉ እንደ ጠጅ አንቡላ ቀስበቀስ ወደ ታች መዝቀጥ ጀመሩ። ከዛም ከወዲያ ማዶ ካለ ተራራ ስር ያለቸው ምንጭ ስትፈስ አዳመጣት ።
"አባ...ምንጩን ሰማሁት " አለ ወጣቱ
"የዜን መግቢያው እሱ ነው አሉት"
በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በዙሪያው ያለውን ህይወት ተረዳ ። አበቦች ፣ መስኩ ፣ ተራራዎች ፣ ወንዙ ፣ የአእዋፍ ዝማሬ ሁሉ ነገር እንደ አዲስ ነገር ተገነዘባቸው ። በህይወቱ ተሰምቶት የማያውቅ ሰሜት ተሰማው። ነፈሱ ረጋች። ብዙም ሳይቆይ ሀሳቦቹ አንሰራርተው አእምሮ በሀሳብ ተሞላ ። ነገሮች ወደ ነበሩት ተመለሱ ።
ፈጣሪ በፈጠረው ነገር ሁሉ ወስጥ ይኖራል ። የምንተነፍሰው አየር ፣ የምንጠጣው ውሀ ፣ የምንበላው ምግብ የምንኖርበት አከባቢ...በኛም ውስጥ ይኖራል ....ልብ ምታችን...ደም ዝውውር ...የተመጠኑ ሆሮሞኖች ወዘተ። ፍጥረት አንድ ትልቅ ኦኬስትራ ባንድ ትመስላለች ሳሩ ደኑ ቅጠሉ አእዋፋት አራዋት ጨረቃና ፀሀይ በአንድ ስልተ- ምት ይፈሳሉ ። የሰው ልጅ የገዛ አእምሮ ሳንካ ሆኖበት ሌላ ስልተ - ምት ይፈልጋል ። ዝና ፣ ገንዘብ ፣ ስልጣን ውስጥ እራሱን ለማግኘት ይሞክራል ። ለምሳሌ ሱናሚ በተከሰተ ጊዜ ገና ከመምጣቱ በፊት እንስሳት ሁሉ የመጣውን አደጋ ተረድተው ወደ ከፍታ ቦታ አሰቀድመው ሸሽተው ነበር። የሰው ልጅ ግን ከተፈጥሮ ስልተ-ምት ወጪ በመሆኑ 150000 የሚሆኑት ዝርያዎቹ ጠፍተዋል ። የፈጠሪና የተፈጥሮ አንድ አካል ነን...ፈጣሪ ሁሉ ነገር ውስጥ ካለ ...ሁሉም ቦታ ካለ....ልክ እንደ ወጣቱ ብርሀነ ህሊናችንን ሳንጠቀምበት ቀርተን ፤ ከስልተ - ምት ወጥተን ሳናስተውለው ቀረን እንጂ እሱ እኮ ሁሌም አለ።
October 6, 2021 16.5K 24