ሕፃናት ዘንድ የፈጣሪ ቁጣ ; ፍርሃት ; ቅጣት ... የሚባል ነገር የለም። ለእነሱ ህይወት በራሷ ምሉዕ እና ትርጓሜም ሆነ መሻት የተሸከመች ባለመሆኗ ፈጣሪን ያለምንም ፍርሃትም ሆነ ጥያቄ ይቀርቡታል።
ታዋቂው የአሜሪካ የመፅሐፍ ቅዱስ ሰባኪ ቢሊ ግርሃም አንድ ቀን ወደ አንዲት ትንሽ የገጠር ከተማ ለስብከት አገልግሎት ይሄዳሉ ። በከተማዋ ደርሰው የአገልግሎት ሰዓታቸው እስኪደርስ ደብዳቤ ለመላክ ፖስታ ቤት ፍለጋ በጎዳና ላይ መዘዋወር ይጀምራሉ። ይሁንና የፖስታ ቤቱ አድራሻ በቀላሉ የሚገኝ አልሆነም።ዶ/ር ቢሊ ግርሃም በዚህ መካከል አንድ የስምንት ዓመት ህፃን በመንገድ ዳር ለብቻው ሲጫወት ይመለከቱትና ወደ እሱ በመሄድ "የኔ ልጅ ስምህ ማነው?" ይሉታል።
ልጁም " ጆን እባላለሁ " ይላል።
" ጆን እባክህ የፖስታ ቤቱ አድራሽ ጠፍቶኝ ተቸግሬያለው። የከተማዋ ፖስታ ቤት የት እንደሆነ ታውቃለህ?" በማለት ይጠይቁታል። ጆንም ቀኝ እጁን ከፊት ለፊቱ በተዘረጋው መንገድ ላይ እየጠቆመ ለዶ/ር ቢሊ ግርሃም የፖስታ ቤቱን አዳራሽ አሳያቸው።
ዶ/ር ቢሊ ግርሃም በዚህ ግዜ ልጁን አመስግነው "ማታ ጎስፔል ባኘቲስት ቤተክርስቲያን በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ሰዎች እንዴት መንግስት ሰማያት መግባት እንደሚችሉ መንገዱን አስተመራለሁና ከቻልክ ከወላጆችህ ጋር እንድትመጣ።" በማለት ይጋብዙታል።
ሕፃኑ ልጅ ግን በማቅማማት ፍላጎትም እንደሌለው አንገቱን በመነቅነቅ እየገለፀ "የምመጣ እንኳን አይመስለኝም " አላቸው።
በጆን ምላሽ የተገረሙት ዶ/ር ቢልግርሃም ለምን መምጣት እንዳልፈለገ ሲጠይቁት ጆን:- " የፖስታ ቤቱን መንገድ የማታውቅ ሰው እንዴት ብለህ ነው የመንግስተ ሰማይን መንገድ የምታሳየኝ ?" በማለት ማጫወቻዎቹን ይዞ ሮጠ።
#ጥበብ ከጺላጦስ
(ኅይለጊዮርጊስ ማሞ) ቅፅ 2
October 6, 2021 14.6K 33