ኮሩ ያሰለጠናቸውን የጤና ሙያተኞችን አስመረቀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮር ለወራት ያሠለጠናቸውን የላብራቶሪ፣ የፋርማሲና የዳታ ሙያተኞችን አስመረቀ።
በምረቃው ወቅት የተገኙት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጤና መምሪያ ሃላፊ ኮሎኔል ፋንታሁን ተፈራ ተመራቂዎች የሠራዊቱን ጤና የምታስጠብቁ ግዳጁን በላቀ ብቃት እንዲፈፅም የምታደርጉ ትልቅ ሚና የምትጫወቱ መሆናችሁን አውቃቹ የወሰዳችሁትን ሥልጠና ወደ ተግባር በመቀየር ተልዕኳችሁን መወጣት አለባችሁ ሲሉ አሥገንዝበዋል።
የኮሩ ሆስፒታል ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ገዛሃኝ ጌታ በበኩላቸው ስልጣኞቹ በቆዩበት የስልጠና ጊዜ መውሰድ የሚገባቸውን ሥልጠና በአግባቡ በቲዮሪና በተግባር መውሰዳቸውን ተናግረው በቀጣይ ከቅድመ መከላከል እስከ ህክምና አገልግሎት መሥጠት የዘለቀ ሙያ መሥጠት እንደሚችሉ ተናግረዋል። የዘገበው ሱማፍ ብርሃኑ ነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
18
11
1September 3, 2026 3.7K