በሁርሶ እጩ መኮንን ማሠልጠኛ ለአሰልጣኞችና ሰልጣኞች ሥልጠና ተሰጠ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም
በሁርሶ እጩ መኮንን ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለሚገኙ አሰልጣኞች እና ሰልጣኝ የእጩ መኮንኖች በሃገረ መንግስት ምስረታና በኢትዮጵያ ወታደራዊ ታሪክ ፤የዘመኑ የወታደራዊ ስነ ልቦና ጦርነት የሳይበር ደህንነት፤ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሠጥቷል።
የዘመኑ የስነ-ልቦና ጦርነት በሚል ርዕስ ትምህርት የሰጡት በመከላከያ የሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ የሰው ሃይል ምዘና መረጣ ኃላፊ ኮሎኔል ታምራት ዘርፉ የዘመኑ ጦርነት ከጦር ሜዳ ባለፈ በሰዎች አእምሮ እና ስነ-ልቦና ላይ እንዴት እንደሚካሄድ፣ እንዲሁም የመረጃ ፍሰትን በመጠቀም ተለዋዋጭ በሆኑ የውጊያ ውሎዎች ውስጥ ጠንካራ የስነ ልቦና ዝግጁነት ማዳበር የውጊያ ብቃትን፣ የውሳኔ ሰጪነት ችሎታንና የወታደራዊ አመራር ጥበብን ለማጎልበት ዋና መሰረት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የሃገረ መንግስት ምስረታና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ታሪክ በሚል ርዕስ ትምህርት የሰጡት በመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ምክትል አዛዥ ለስርዓተ ትምህርት ዕድገት ጥናትና ምርምር ዲን ዶክተር ደምሌ ሞላው የሃገረ መንግስት ግንባታ ታሪካዊ ሂደትና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ታሪክ አመሰራረትና የነፃነት የማስከበር ጉዞ የነፃነትና የጀግንነት ምሳሌ መሆኑን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር አያይዘው በጀግንነት እሴቶችና በሠራዊቱ ታሪካዊ ሚና ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የሰው ሰራሽ አስተውሎት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት የሰጡት በመከላከያ ሳይበር ማዕከል የሳይበር መከላከል መምሪያ ሃላፊ ኮሎኔል ንጋቱ በቀለ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳብና ወቅታዊ አስፈላጊነቱ ላይ በውጊያ ውሳኔ አሰጣጥ፣ በቅድመ መረጃ ስብሰባ፣ በመረጃ ትንተና ላይ የሚያመጣውን አብዮታዊ ለውጥ በተመለከተ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።
የሳይበር ደህንነት ትምህርት የሰጡት ሻለቃ ይርጋለም ሀይሉ፣ በቴክኖሎጂ በረቀቀው የኢንፎርሜሽን ዘመን የሳይበር ምህዳር አምስተኛው የጦርነት ሜዳ በመሆኑ፤ የወታደራዊ መረጃ መረቦችን መከላከልና ሊሰነዘሩ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን ቀድሞ ማክሸፍ የሃገርን ደህንነት ለማረጋገጥ የማያወላውል ቅድመ ሁኔታ የሚተነትን መኮንን መገንባት አሰፋላጊ እንደሆነ አሥረድተዋል።
ዘጋቢ ውብሊቀር ደሳለው
ፎቶግራፍ ታማራት ጌቱ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
20
9September 4, 2026 3.4K 1