ተልዕኮ ተኮር የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ የድል መሰረት መሆኑ ተገለፀ። ‎የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

ተልዕኮ ተኮር የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ የድል መሰረት መሆኑ ተገለፀ።

‎የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

‎የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ክፍል ለዕዙ የሠራዊት ክፍሎች በቀጣይነት ሊያጋጥሟቸው ለሚችሉ ማንኛውም ግዳጆች የሚያበቃ የሞራልና ስነ-ልቦና ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል።

ሀገራዊ እና ተቋማዊ እሴቶችን መሰረት ያደረጉ የእለት ተእለት የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ማካሄድና ሊያጋጥሙ ለሚችሉ ትንኮሳዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ብቁ ኃይል መገንባት በየደረጃው የሚገኙ መሪዎች ዋና ተግባር መሆኑ በስልጠናው ተገልጿል።

ወቅታዊና የይሆናል ተልዕኮን መሰረት ያደረጉ የእለት ተእለት  የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ስራዎች የድል መሰረቶች በመሆናቸው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በተከታታይነት መከናወን ይኖርባቸዋልም ተብሏል።

ስልጠናው በዕዙ ስር በሚገኙ ኮሮች የግዳጅ ቀጣና በመዘዋወር የሚሰጥ ሲሆን የሠራዊቱን ሞራል በማነሳሳት እና የአሸናፊነት ስነ-ልቦና በመገንባት በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ መሰናክሎች ሳይበገር ግዳጁን በጀግንነት መፈፀም የሚችል ጠንካራ ሠራዊት የመገንባት አላማ ያለው መሆኑን የዕዙ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ኃላፊ ኮሎኔል አበበ መለሰ አብራርተዋል።

ዕዙ ደማቅ የጀግንነት ታሪክ ያስመዘገበ የሕዝብ ልጆች መገኛ መሆኑን ያወሱት ኃላፊው ፣ አሁንም የፅንፈኛውን ቡድን እኩይ ዓላማና አፍራሽ የጥፋት ሴራዎችን በመበጣጠስ ረገድ በአስተማማኝ የዓላማ ፅናት እና በጠንካራ የስነ-ልቦና ዝግጁነት ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ  ስልጠናው ሠራዊቱ የነበረውን የጋራ አንድነት ከማጠናከር በተጨማሪ የፅንፈኛውን ቡድን የውሸት ፕሮፖጋንዳና አጥፊ አስተሳሰቦች በንቃት እየመከቱ አካባቢውን ከማንኛውም ወታደራዊ ስጋት ለመጠበቅ ትልቅ ወኔና አቅም ይፈጥራል።

የሠራዊት አባላቱ  በስልጠናው ያገኟቸውን ጠንካራ የስነ-ልቦና ስንቅ፣ የዓላማ ፅናትና እውቀቶች በተግባራዊ ግዳጅ  እንደ ዋና አቅም ሊጠቀሙት ይገባል ያሉት ኮሎኔል አበበ መለሰ የተቋሙን ወታደራዊ እሴቶችና የድል አድራጊነት ስሜት ጠብቀው የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት በታማኝነት እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

‎ዘጋቢ ሳሙኤል  ምሴ
‎ፎቶግራፍ ሁንያለው ፈጠነ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍24❤8👏4😁3🔥2
September 4, 2026 2.7K