ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ መከላከያ እንደ ተቋም ተሸላሚ ሆኗል፡፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ መከላከያ እንደ ተቋም ተሸላሚ ሆኗል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

የመከላከያ ስነ-ምግባር መከታተያ መምሪያ ከፌደራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከነሃሴ 27 እስከ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሶስት ቀናት ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ እቅድ እና ሪፖርት ዝግጅት ክትትል ዳይሬክተር ኮሎኔል ፈይሳ ታደሰ  መከላከያ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ላሳየው ትጋት እና ቁርጠኝነት በሀገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጅ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል በአንድ ወቅት ብቻ ተሰርቶ የሚጠናቀቅ የአጭር ጊዜ ተግባር ባለመሆኑ በየጊዜው በአባላቱ ዘንድ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ በቅንጅት እና በመዋቅር ተደራጅቶ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ ስልጠናው የሀብት ብክነትን ለመቀነስ እና አበላቱን በስነ-ምግባር ለመገንባት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

የመከላከያ ስነ-ምግባር መከታተያ መምሪያ ሃላፊ ተወካይ ኮሎኔል ሲሳይ ተስፋሁን በበኩላቸው ተቋማችን መከላከያ ከተሰጠው የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ እና ሀገርን የመጠበቅ ሃለፊነት አንፃር ስነ-ምግባር፣ የዓላማ ፅናት እና ዲሲፕሊን የማይታጠፉ መሰረቶቻችን ናቸው ብለዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የፌዴራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያዎች አቶ የኋላሸት ደሳለኝ እና ወይዘሮ ሜሮን ዳምጤ ስልጠናው በሰልጣኞች ላይ ተጨባጭ የእውቀት፣ የክህሎት እና የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

መከላከያ ህዝብን እና ሀገርን በነፍሱ የሚያገልግል ሰራዊትን የሚመራ ተቋም በመሆኑ ጠላትን በጥይት ፊት-ለፊት ከመፋለም ባልተናነሳ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መጋፈጥ እንዲችል ስልጠናው የጎላ ሚና አለው ብለዋል፡፡

ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶግራፍ እፀገነት ዴቢሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤15
September 4, 2026 1.9K 4