ዕዙ ለተማሪዎች ስድስት መቶ ደርዘን ደብተር ድጋፍ አደረገ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 29 ቀን 2019 ዓ.ም
ለሀገር ሉዓላዊነት ዘብ ስንቆም ትውልዱ በእውቀት እንዲሻገር ግዴታችንን መወጣት አለብን በሚል ሰዋዊ እሳቤ የ11ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የሠራዊት አባላት በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ለሚገኙ የአዲስ አለም (ቀበሌ 03) እና የበኬ (ቀበሌ 05) ታዳጊ 913 ተማሪዎች 600 ደርዘን ደብተር እና እስክርቢቶ ድጋፍ አድርገዋል።
በዚሁ የመልካምነት መገለጫ በሆነው ስነ-ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የ11ኛ ዕዝ ሎጅስቲክስ ሃላፊ ኮሎኔል እሸቱ ከበደ፤ መከላከያ ሠራዊት አገር ከመጠበቅ ባሻገር ህዝባዊነቱን በተግባር እያሳየ የመጣ ህዝባዊ ሰራዊት መሆኑን ጠቁመው ይህን ደማቅ ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል በዛሬው ዕለት ለቃሉ ወረዳ ታዳጊ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።
የ11ኛ ዕዝ አዛዥ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ደሳለኝ አደመ በበኩላቸው፤ ዕዙ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ህዝባዊ ድጋፎችን ሲያበረክት መቆየቱን አስታውሰው፤ የዛሬው የደብተር እና እስክርቢቶ ስጦታም የዚሁ ህዝባዊ አደራ አካል መሆኑን ገልጸዋል።
የቃሉ ወረዳ አስተዳደር ተወካይ አቶ ጀማል መሃመድ በሰጡት አስተያየት፤ ሠራዊታችን ምንጊዜም ህዝባዊነቱን በተግባር እያሳየ መምጣቱን ተናግረው ዛሬ ለአዲስ አለም እና በኬ ቀበሌ ህፃናት የተደረገው ድጋፍ ሠራዊቱ ተዋጊ ብቻ ሳይሆን በልማቱ መስክ እየተሳተፈ ህይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ ሥለመሆኑ አንስተዋል።
የሁለቱም ቀበሌ ሊቀመንበሮች እና የአካባቢው ማህበረሰብ ሠራዊቱ በችግራችን ጊዜ ከጎናችን መሆናቸውን በተለያዬ መንገድ እያረጋገጠልን ይገኛልና ታላቅ ክብርና ምስጋና አለን ብለዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
8September 4, 2026 1.6K