ዕዞች ለፋይናንስ ስራ አመራር እና ለመገናኛ ሙያተኞች ስልጠና ሰጡ፡፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 29… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

ዕዞች ለፋይናንስ ስራ አመራር እና ለመገናኛ ሙያተኞች ስልጠና ሰጡ፡፡
          
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም
 
በምስራቅ ዕዝ ከሚገኙ ሁሉም ኮሮች እና ዕዝ ስታፍ የተውጣጡ የፋይናንስ፣ የበጀት፣ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ሙያተኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ከመከላከያ ግዥ መምሪያ ጋር በመተባበር ለሳምንታት ሲሰጥ የቆየው ሙያዊ ስልጠና ሲጠናቀቅ የተገኙት የምስራቅ ዕዝ ግዥ ኃላፊ ኮሎኔል አለማየሁ ሞሊቶ  ስልጠናው በዋናነት የግዥ፣ የፋይናንስ እና የንብረት አስተዳደር ሥራዎችን ዘመናዊ ቀልጣፋ እንዲሁም ከእጅ ንክኪ የፀዳ አድርጎ ለመተግበር የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አሰራሩ ከአሁን በፊት ከነበረው እጅግ በተሻለ ሁኔታ ግልፅነት እና ተጠያቂነት ሊያሰፍን የሚችል በመሆኑ በግዥ ተገዝተው ለሠራዊቱ አገልግሎት የሚውሉ ንብረቶች ህጋዊ መሆናቸውን ሊያሳዩ የሚችሉ የኦንላይን አሰራሮች መዘርጋታቸው ትክክለኛነትን የሚያረጋግጡ  መሆናቸውን ተናግረዋል።

ህጋዊ እና ዘመናዊ በሆነ መልኩ በፍጥነት ክፍያ እንዲከናወን ማድረግ የሚችል እንዲሁም ተገዝተው የሚገቡ ንብረቶች አስፈላጊው ዶክመንት እና የጥራት ሁኔታን በማረጋገጥ ለተጠቃሚ ክፍሎች ለማሰራጨት የሚያስችል አቅም የተገኘበት ስልጠና እንደሆነም አሥረድተዋል፡፡

በመከላከያ ግዥ መምሪያ የውጭ ግዥ ዴስክ አስተባባሪ ሻለቃ ማስተዋል ጌትነት በበኩላቸው በመከላከያ ደረጃ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ አዳዲስ የግዥ፣ የፋይናንስ፣ የበጀት እንዲሁም የንብረት አጠቃቀም መመሪያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ምስራቅ ዕዝ ያሳየው ተነሳሽነት የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል። ዘገባው የምስራቅ ዕዝ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ነው፡፡

በተመሳሳይ የ6ኛ ዕዝ አዋሽ ኮር ከክፍለጦሮች ከመከላከያ ውጊያ ምህንድስና የተውጣጡ አዳዲስ የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ሲግናል ባለሙያዎችን ለወራት ያሕል በጥራት አሰልጥኖ አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአዋሽ ኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጋዲሳ ዲሮ ሰልጣኞቹ በስልጠና ያገኙትን አቅም ተጠቅመው ለተቋማዊ ለውጡ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት የሙያ ሥነ-ምግባርን በመጠበቅ፣ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በታማኝነትና በብቃት እንዲወጡ አሳስበዋል።

ሥልጠናውን በስኬት ያጠናቀቁ የመገናኛ ባለሙያዎች በቀጣይ በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደተግባር እንዲለውጡ መልእክት አስተላልፈዋል። የዘገበው አብርሐም ሙሉአለም ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤9👍3
September 4, 2026 1.2K 1