የኢትዮጵያ መከላከያ ሀገራዊ የሪፎርም ስኬቶች
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም
በማንኛውም ሀገር የመንግሥትነት፣ የሉዓላዊነት እና የደኅንነት መሠረት የመከላከያ ሠራዊት ነው። ወቅቱ የሚጠይቀውን ፈጣን የቴክኖሎጂ ዕድገት፣ የጂኦፖለቲካዊ ለውጦች እና ዘመናዊ የደኅንነት ስጋቶችን ለመቋቋም የተከናወኑት ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች የሀገራችንን የመከላከያ አቅም ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግረውታል።
ተቋሙ ካከናወናቸው የሪፎርም ሥራዎች በዋናነት ትኩረታቸውን ያደረጉት ከፍተኛ ጥራት ያለው፣ በሙያዊ ብቃት የዳበረ፣ ለሕግ እና ለሕዝብ የወገነ እንዲሁም ዘመናዊ እና ዘላቂ አቅም ያለውን የመከላከያ ሠራዊት በመገንባት ላይ ነው።
የዚህ ሪፎርም ዋነኛ ስኬት ሠራዊቱ ከማንኛውም ፓርቲ እና ፖለቲካ ወገኝተኝነት ነፃ ሆኖ፣ ሕገ-መንግሥታዊ እና ሀገራዊ ማዕቀፍን ብቻ ተከትሎ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ነው።
የሠራዊቱ አባላት እና አመራሮች እድገት እና ስምሪት በብቃት፣ በትምህርት ዝግጅት፣ በሥነ-ምግባር እና በውጤታማነት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዲሆን ተደርጓል።
ዘመናዊ ጦርነት በመሣሪያ ብዛት ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂ እና በመረጃ የበላይነት የሚወሰን በመሆኑ፣ የመከላከያ አየር ኃይልን በዘመናዊ የውጊያ ቴክኖሎጂዎች፣ የሰው አልባ አውሮፕላኖች እና በሳይበር ደኅንነት ማጠናከር ተችሏል።
የመከላከያ ኢንዱስትሪዎች እና የምርምር ተቋማት አቅም እንዲያድግ በማድረግም ከውጭ ጥገኝነት የመውጣት አቅም ተፈጥሯል።
ሠራዊቱ በውጊያም ሆነ በሰላም ማስከበር ወቅት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሕጎችን በጥብቅ እንዲከተል የስልጠና ተቋማት እና አካዳሚዎች መዋቅር ተሻሽሏል።
እነዚህ የሪፎርም ሥራዎች በተቋማዊ ሕጎች እንዲደገፉ በመደረጉ፣ የመከላከያ ሠራዊታችን የሀገርን ሉዓላዊነት አስተማማኝ በሆነ መንገድ ማስጠበቅ የሚችል፣ የቴክኖሎጂ ባለቤት የሆነ እና በቀጣናው እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነ ዘመናዊ ተቋም እንዲሆን አስችለውታል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
17
1September 4, 2026 2.9K