የጣርማበር - መለያያ ሰፌድ ሜዳ የጠጠር መንገድ ጥገና እየተካሄደለት ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21/2018 (ኢመአ)፦ ከጣርማበር መለያያ እስከ ሰፌድ ሜዳ ለሚዘልቀው የጠጠር መንገድ ጥገና እየተደረገለት ይገኛል። ጥገናው የሕዝቡን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል ታስቦ በትኩረት እየተከናወነ ያለ ሥራ ነው።
ይህ አጠቃላይ 118 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የመንገድ ፕሮጀክት፣ ከዚህ ቀደም በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አማካኝነት ግንባታው ሲካሄድ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሳይጠናቀቅ ተስተጓጉሎ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት ግን ለትራንስፖርት እጅግ አስቸጋሪ በሆነው 21.6 ኪሎ ሜትር የመንገዱ ክፍል ላይ ሰፊ የጥገና ሥራ እየተሠራ ይገኛል።
እስካሁንም በማሽን የቦይ ማጽዳት፣ የድንጋይ ሙሌት፣ በጭቃ የተበላሹ አካባቢዎችን የማስወገድ እንዲሁም በግሬደር የመንገዱን አካል የማስተካከልና የማጠናከር ሥራዎች ተከናውነዋል። የጥገና ሥራውን የኢመአ የዓለምገና መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በራስ ኃይል እያከናወነው ሲሆን፣ የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ደግሞ የዓለምገና መንገድ ኔትወርክ ማኔጅመንት ቅርንጫፍ ቢሮ በበላይነት እየተከታተለው ነው።
የዚህ መንገድ መጠገን ማኅበረሰቡን ለእንግልትና ለትራንስፖርት መጉላላት ከዳረጉ ችግሮች የሚያላቅቅ ሲሆን፣ የትራፊክ አደጋን ከመቀነስና ጊዜን ከመቆጠብ ባሻገር የግብርና ምርቶችንና የተለያዩ ግብዓቶችን ወደ ገበያ ለማቅረብ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
በቀጣይም ከዚህ ቀደም ይስተዋሉ የነበሩ ማነቆዎችን በመቅረፍ ሙሉ የግንባታ ሒደቱን በቀጣዩ በጀት ዓመት ለማቀላጠፍ በትኩረት እየተሠራ ነው።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
5
5August 27, 2026 2.9K 9