ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር: post #4872 — TG.ME

9ኛው የመንገድ ጥናትና ሥርፀት ኮንፈረንስ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም(ኢመአ): የመንገድ ልማትና አስተዳደር ሥራዎችን በሳይንሳዊ ምርምርና በቴክኖሎጂ ለማገዝ የተዘጋጀው 9ኛው የመንገድ ጥናትና ሥርፀት ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አብዱራህማን፣ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሂሩት ዮሐንስ እና የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወልደገብርኤልን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል።

ባለፉት ስምንት ዓመታት የተካሄዱት ተከታታይ የምርምር ኮንፈረንሶች በሀገሪቱ የመንገድ ልማት ላይ ውጤታማ ለውጦችን ማምጣት ችለዋል። በአሁኑ 9ኛ ኮንፈረንስም በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን፣ ተያያዥ አውደርዕይም ተካሂዷል። በጥናቶቹ በሌሎች አገራትና ፕሮጀክቶች ላይ ተተግብረው ውጤታማ የሆኑ የመንገድ ግንባታና አስተዳደር ልምዶች የተዳሰሱ ሲሆን፣ እነዚህ ተሞክሮዎች ለሀገሪቱ የመሠረተ ልማት ዕድገት አዳዲስ ዕድሎችን ይዘው ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተለይም በአሁኑ ወቅት በዘርፉ ላይ ፈተና እየሆኑ ያሉትን እንደ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ እና የመንገድ መሸራተት (ናዳ) ያሉ ዋና ዋና ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ተግባራዊ የመፍትሔ ሐሳቦች በኮንፈረንሱ ላይ በስፋት ተመክሮባቸዋል። ከተቀመጡት የመፍትሔ አቅጣጫዎች መካከልም ዘላቂነትን ለማረጋገጥ በሲሚንቶ ኮንክሪት በሚሠሩ መንገዶች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሠራ በጥናት ተመልክቷል።

በመድረኩ የተሳተፉ ባለሙያዎች በኮንፈረንሱ ያገኟቸውን አዳዲስ ዕውቀቶች፣ ቴክኖሎጂዎችና ፈጠራዎች በመጠቀም በመንገድ ግንባታ፣ ዲዛይን፣ ጥገና እና አስተዳደር ሥራዎች ላይ የላቀ ሙያዊ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ተብሎ ይታመናል።

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
❤6
August 28, 2026 2.4K 3 4