የኦሞራቴ–ኛንጋቶም የ63.5 ኪሎ ሜትር አስፋልት መንገድ ግንባታ 85 በመቶ ደረሰ
ጂንካ፣ ነሐሴ 04/2018 (ኢ መ አ):- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገነባውና ኦሞራቴን ከኛንጋቶም ወረዳ መስተዳድር ካንጋተን ጋር የሚያገናኘው የ63 ነጥብ 52 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 85 በመቶ ደርሷል።
965 ሚሊዮን ብር (ብር 900,000,000.00) የሚፈጀው ይህ ፕሮጀክት ግንባታው በኤን.ኬ.ኤች (NKH) ኮንስትራክሽን እየተከናወነለት የሚገኝ ሲሆን፣ የሳውንድ ኢንጅነሪንግ ሶሊሽን እና ፒዩር ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ ጥምረት ደግሞ በአማካሪነት እየሰሩበት ይገኛል።
እስካሁን በተከናወነው ስራ 32.45 ኪሎ ሜትር አስፋልት የመንጠፍ፣ 62.97 ኪሎ ሜትር የአፈር ሙሌት፣ 155 አነስተኛ እንዲሁም 38 መካከለኛ የውሃ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ግንባታ ተጠናቋል። በቀጣይም ቀሪ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በትኩረት እየተሰራ ነው።
የመንገድ ፕሮጀክቱ በስራ ሂደቱ ላይ ከታችኛው የኦሞ ስምጥ ሸለቆ መካነ-ቅርስ ጥበቃ ጋር በተያያዘ የወሰን ማስከበር፣ የድንጋይና የአፈር ማውጫ ቦታዎች እንዲሁም የመተላለፊያ መስመሮች ለውጥ ያጋጠሙ ችግሮች ናቸው። ይህንን ችግር ለመፍታት ከባህልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ጋር በመመካከር የቅርስ ሁኔታን የሚያጠና ባለሙያ ተቀጥሮ መፍትሄ እንዲያገኝ ተደርጓል። በተጨማሪም በኦሞራቴ ከተማ የነበረው የወሰን ማስከበር የካሳ ክፍያ መዘግየት ችግር በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ተፈቷል።
ከዚህ ቀደም አካባቢዎቹን የሚያገናኝ ቀጥተኛ የመኪና መንገድ ባለመኖሩ፣ ነዋሪዎች በቱርሚ ከተማ በኩል ከ140 ኪሎ ሜትር በላይ ተጨማሪ ርቀት ለመጓዝና ከ4 ሰዓታት በላይ ለማባከን ይገደዱ ነበር። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ይህንን እንግልት በእጅጉ ከመቀነሱም በላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን ያቀላጥፋል። ከዚህ ባለፈም የኦሞራቴ እና የኛንጋቶም ማህበረሰቦችን በማገናኘት፣ የአካባቢውን የእንስሳት ሀብት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ፣ የንግድ ፍሰቱን ለማሳደግ እና የታችኛው የኦሞ ስምጥ ሸለቆ መካነ-ቅርስን የቱሪዝም ተደራሽነት ለማሳደግ ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል።
ኢትዮጵያን የማገናኘት 75 ዓመታት
መንገዳችን፤ ኃላፊነታችን!
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
9
4August 10, 2026 5.2K 12