ዩኒቨርስቲዎች ሀገርን የሚያሻግሩ የእውቀት ማዕከላት ሊሆኑ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ገለጹ፤
---------------------- // ---------------------
(ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም) ዩኒቨርስቲዎች ሀገርን የሚያሻግሩ የእውቀት ማዕከላት ሊሆኑ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር ባደረጉት የምክክር መድረክ አስገነዘቡ።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ በንግግራቸው፤ ዩኒቨርስቲዎች የሙያና የስነ-ምግባር እሴቶች የሚገነቡባቸው የአካዳሚክና የምርምር ተቋማት መሆናቸውን ገልጸው የህብረተሰቡ የሞራልና የእውቀት መሪዎች በመሆናቸው፣ የሙያ ስነ-ምግባርንና የሞራል እሴቶችን በመላበስ ማህበረሰቡን በእውቀትና በሙያ ሊደግፉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
አክለውም፤ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስብጥር ብዝሃነትን ባካተተ፣ መተዋወቅን፣ መከባበርን፣ መቻቻልንና ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ በዩኒቨርስቲዎች ከተማሪዎች ምደባና ዝውውር ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር በቴክኖሎጂ የታገዘ አዲስ የአሰራር ስርዓት እንደሚዘረጋ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ከበጀት አጠቃቀም ረገድም ተቋማቱ የተመደበላቸውን በጀት ለታቀደለት ዓላማ ብቻ በቁጠባና በተጠያቂነት መንፈስ ማዋል እንዳለባቸው አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://web.facebook.com/share/p/1EPYjkE9WK/
September 3, 2026 20.5K 16


