በሀገር አቀፍ ደረጃ ፍትሃዊና ወጥነት ያለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የደረጃ እድገት ሥርዓት ለመገንባት እየተሠራ ነው።
---------------------- // --------------------------
(ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን፣ ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና ከሸያሾኔ ተቋም ጋር በመተባበር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ሥራተኞች የደረጃ እድገት መመሪያን ለማሻሻል የሚያስችሉ ግብዓቶች የሚሰበሰቡበት የምክክር መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ መክፈቻ ላይ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሚጀና እንደገለጹት በሀገር አቀፍ ደረጃ ፍትሃዊና ወጥነት ያለው የመምህራን የደረጃ እድገት ሥርዓት ለመገንባት በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
መምህራን መስፈርቱን አሟልተው እድገት ሲጠይቁ ያለምንም አድሎና እንግልት በወቅቱ ማግኘት እንዳለባቸው ያሳሰቡት ዶ/ር ኤባ የመመሪያው መሻሻል ዋና ዓላማ አፈጻጸሙን ወጥ ማድረግ፣ ግልጽነት መፍጠር እና መመሪያውን ዘላቂና ተራማጅ ማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተጠባባቂ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰራዊት ሀንዲሶ ከሁለት ዓመት በፊት በሥራ ላይ የነበረው የቀድሞ መመሪያ 12 ሥርዓታዊና በርካታ የአተገባበር ችግሮች የነበሩበት፣ እንዲሁም ለተለያዩ ትርጉሞች የተጋለጠ እንደነበር አስታውሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1DRF9hbYNm/
September 3, 2026 20.8K 9




